From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
ተስፋህ ፡ ጨልሞ ፡ ጭንቀት ፡ አስጥሞህ
መጥፋትህ ፡ ታይቶኝ ፡ ከዚያ ፡ ጣር ፡ አውጥቼህ
ዳን ፡ ብለህ ፡ ነበር ፡ አግኝተህ ፡ እፎይታ
ለምን ፡ ነው ፡ ዛሬ ፡ የሆንከው ፡ ከርታታ
አዝ፦ ተመለስ ፡ ተምለስ ፡ ተመለስ ፡ ልጄ ፡ ሆይ (፪x)
በእኔ ፡ ተማምነህ ፡ ስትመላለስ
በእንባ ፡ ጸሎት ፡ ቀርበህ ፡ ስትታደስ
የነበረህ ፡ ወዝ ፡ መልክህስ ፡ የት ፡ አለ
ናና ፡ ታረቀኝ ፡ ፀጋዬ ፡ እያለ
አዝ፦ ተመለስ ፡ ተምለስ ፡ ተመለስ ፡ ልጄ ፡ ሆይ (፪x)
የፍቅርን ፡ ወንጌል ፡ ለሌላው ፡ ሰብከህ
ሸክማቸውን ፡ ከብደህ ፡ ለጠፉት ፡ አልቅሰህ
መስክረህ ፡ ወደ ፡ ሕይወት ፡ አምጥተህ
ላይህ ፡ አዝናለሁ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ ኮብልለህ
አዝ፦ ተመለስ ፡ ተምለስ ፡ ተመለስ ፡ ልጄ ፡ ሆይ (፪x)
ቤቴ ፡ ናፍቆህ ፡ ብትመለስልኝ
ይቅርታ ፡ ፈልገህ ፡ ብትመጣልኝ
የምህረት ፡ እጁስ ፡ ተዘግታለች
የፍቅር ፡ አምባም ፡ ዐይኔም ፡ ታፈሳለች
አዝ፦ ተመለስ ፡ ተምለስ ፡ ተመለስ ፡ ልጄ ፡ ሆይ (፪x)
|