ጥልቅ ፡ ሆይ ፡ ከፀጋህ ፡ አምላኬ (Telq Hoy Ketsegah Amlakie)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

1. ወደ ፡ አምላኬ ፡ ልብ ፡ የሚያደርስ
አንድ ፡ ቅዱስ ፡ ደጅ ፡ አውቃለሁ
ከዚያም ፡ ደግ ፡ ብርሃን ፡ ሲሰርጽ
መድሃኒቴን ፡ አያለሁ

አዝ፦ ጥልቅ ፡ ሆይ ፡ ከፀጋህ ፡ አምላኬ
ያ ፡ ደጅ ፡ ተከፈተ ፡ ለእኔ
ለእኔ ፡ ለእኔ
ተከፍቶልኛል

2. ተከፈተ ፡ ለሁሉ ፡ ሰው
ሊገቡት ፡ ለሚወዱ
ለንጉሥም ፡ ለባርያም
ለምድር ፡ ወገን ፡ ሁሉ

አዝ፦ ጥልቅ ፡ ሆይ ፡ ከፀጋህ ፡ አምላኬ
ያ ፡ ደጅ ፡ ተከፈተ ፡ ለእኔ
ለእኔ ፡ ለእኔ
ተከፍቶልኛል

3. ስለዚህ ፡ ሂድ ፡ ወደርሱ ፡ ደጅ
በዚህ ፡ ግባ ፡ ሳይዘጋ
ዘውድ ፡ ለመቀበል ፡ ተዘጋጅ
የአምላካችን ፡ ፀጋ

አዝ፦ ጥልቅ ፡ ሆይ ፡ ከፀጋህ ፡ አምላኬ
ያ ፡ ደጅ ፡ ተከፈተ ፡ ለእኔ
ለእኔ ፡ ለእኔ
ተከፍቶልኛል

4. በሠማያዊ ፡ ደጅ ፡ አንድ ፡ ቀን
ከመስቀል ፡ ልንፈታ
የሕይወት ፡ አክሊል ፡ ልንጭን
ኢየሱስን ፡ ልናከብር

አዝ፦ ጥልቅ ፡ ሆይ ፡ ከፀጋህ ፡ አምላኬ
ያ ፡ ደጅ ፡ ተከፈተ ፡ ለእኔ
ለእኔ ፡ ለእኔ
ተከፍቶልኛል