ጠላቴ ፡ ቅስሙ ፡ ተሰበረ (Telatie Qesmu Tesebere)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

1. መስሎት ፡ ነበር ፡ ጠላቴ ፡ እኔን ፡ የሚያሸንፈኝ
ብዙ ፡ ጣረ ፡ ደከመ ፡ ከሩጫዬ ፡ ሊያስቀረኝ
መስቀሉ ፡ ጉልበቴ ፡ ሆነ
ሃሳቡ ፡ ተበታተነ ።

አዝ፦ ጠላቴ ፡ ቅስሙ ፡ ተሰበረ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ስሙ ፡ ከበረ
እኔም ፡ ላመስግነው ፡ በደስታ
እስራቴም ፡ ተፈታ ።

2. አምላኬ ፡ ጋሻዬ ፡ ነው ፣ በስሙ ፡ ታምኛለሁ
ጠላቴ ፡ ደስ ፡ አይበልህ ፣ ብወድቅም ፡ እነሳለሁ
ለእጄ ፡ ምርኩዝ ፡ ሆኖኛል
በክንዱም ፡ ይጋርደኛል ።

አዝ፦ ጠላቴ ፡ ቅስሙ ፡ ተሰበረ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ስሙ ፡ ከበረ
እኔም ፡ ላመስግነው ፡ በደስታ
እስራቴም ፡ ተፈታ ።

3. ደሙ ፡ በመቃኔ ፡ ላይ ፡ ምልክት ፡ ሆኖኛል
መቅሰፍት ፡ ወደ ፡ ቤቴ ፡ እንዳይቀርብ ፡ ታድጐኛል
በኩር ፡ የሆነው ፡ ኢየሱስ
የታረደ ፡ እኔን ፡ ሊቀድስ ።

አዝ፦ ጠላቴ ፡ ቅስሙ ፡ ተሰበረ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ስሙ ፡ ከበረ
እኔም ፡ ላመስግነው ፡ በደስታ
እስራቴም ፡ ተፈታ ።

4. ሆሳዕና ፡ እያልኩ ፡ ወዳገሬ ፡ እገባለሁ
የተስፋይቱን ፡ ምድር ፡ በሙላት ፡ እወርሳለሁ
የርስቱ ፡ ተካፋይ ፡ ሆኜ
እኖራለሁ ፡ በእርሱ ፡ ታምኜ ።

አዝ፦ ጠላቴ ፡ ቅስሙ ፡ ተሰበረ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ስሙ ፡ ከበረ
እኔም ፡ ላመስግነው ፡ በደስታ
እስራቴም ፡ ተፈታ ።