ጠላቴ ፡ ሆይ (Telatie Hoy)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ብወድቅ ፡ እነሳለሁኝ
በጨለማ ፡ ብቀመጥ ፡ እንኳን ፡ እግዚአብሔር ፡ ብርሃን ፡ ይሆንልኛል
ስለዚህ ፡ ስለዚህ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ አይበልህ

1. የወይኑ ፡ ፍሬ ፡ ተለቅሞ ፡ እንደቀረው ፡ ቃርሚያ
ደርቄ ፡ ቆሜያለሁ ፡ እኔ ፡ ከበረከትህ ፡ በስቲያ
የሃዘን ፡ እንጉርጉሮ ፡ የምሬት ፡ ለቅሶዬ
አምላኬ ፡ ፊት ፡ እለቃለሁ ፡ እንዲያያት ፡ ሕይወቴን

አዝ፦ ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ብወድቅ ፡ እነሳለሁኝ
በጨለማ ፡ ብቀመጥ ፡ እንኳን ፡ እግዚአብሔር ፡ ብርሃን ፡ ይሆንልኛል
ስለዚህ ፡ ስለዚህ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ አይበልህ

2. በእግዚአብሔር ፡ ላይ ፡ ኀጢአትን ፡ ሰርቻለሁና
ቁጣም ፡ ለቅጣቴ ፡ ሆኖ ፡ ነዶብኛልና
ወደ ፡ ብርሃን ፡ እስኪያወጣኝ ፡ እታገሳለሁኝ
ፈውሶ ፡ እስኪምረኝ ፡ ድረስ ፡ እጠብቀዋለሁ

አዝ፦ ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ብወድቅ ፡ እነሳለሁኝ
በጨለማ ፡ ብቀመጥ ፡ እንኳን ፡ እግዚአብሔር ፡ ብርሃን ፡ ይሆንልኛል
ስለዚህ ፡ ስለዚህ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ አይበልህ

3. በእኔና ፡ በአምላኬ ፡ መሃል ፡ የሚኖረውን ፡ ጉዳይ
ኢየሱስ ፡ ይፈጽመዋል ፡ የመሰረቱ ፡ ድንጋይ
ስለዚህ ፡ ጠላቴ ፡ ወግድ ፡ ጌታ ፡ ይገስጽሽ
አሁንም ፡ ቢሆን ፡ ልጁ ፡ ነኝ ፡ ተረዳ ፡ ከልብህ

አዝ፦ ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ብወድቅ ፡ እነሳለሁኝ
በጨለማ ፡ ብቀመጥ ፡ እንኳን ፡ እግዚአብሔር ፡ ብርሃን ፡ ይሆንልኛል
ስለዚህ ፡ ስለዚህ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ አይበልህ

4. ለዘለዓለም ፡ አይቆጣም ፡ ምህረትን ፡ ይወዳል
የጠላቴን ፡ ምኞት ፡ ቆርጦ ፡ ሴራውን ፡ ያቆማል
የውርደት ፡ ማቄ ፡ ተቀዶ ፡ ነጭ ፡ ልብስ ፡ ለብሼ
ዳግም ፡ እዘምራለሁ ፡ ለእርሱ ፡ ክንዱን ፡ ተንተርሼ

አዝ፦ ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ብወድቅ ፡ እነሳለሁኝ
በጨለማ ፡ ብቀመጥ ፡ እንኳን ፡ እግዚአብሔር ፡ ብርሃን ፡ ይሆንልኛል
ስለዚህ ፡ ስለዚህ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ አይበልህ