ትጉ ፡ አድርገኝ (Tegu Adregegn)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ጊዜ ፡ እንዳይጠፋ ፡ ትጉ ፡ አድርገኝ
ኃጥያተኛ ፡ አይሙት ፡ ተስፋ ፡ ሳያገኝ
እንዴት ፡ ሥራ ፡ ልፍታ?
ክርስቶስን ፡ ያወቅሁ
ፍቅርህን ፡ እንድነግር
ትጋትን ፡ ስጠኝ

ለጠፉት ፡ በጐችህ ፡ ጠባቂ ፡ አድርገኝ
እነሱን ፡ በማሰብ ፡ ፈልጌ ፡ ላገኝ
ባጥር ፡ በጐዳና ፡ ባገር ፡ በባሕር
ለጠፉቱ ፡ ኃጥአን
አድርገኝ ፡ መምሕር


የፍቅር ፡ ምሥጋና ፡ ላቅርብ ፡ ለጌታ
ሥጦታንም ፡ ደግሞ ፡ ለፈጣሪዬ
ስለ ፡ ፀጋውም ፡ ሁሉ ፡ ፀሎት ፡ ላቅርብ
በሥራዬ ፡ ሁሉ
እርሱን ፡ ደስ ፡ ላሰኝ

ንጽሕናን ፡ ስጠኝ ፡ ኃጥያትን ፡ ልጥላ
ውስጡ ፡ ሰውነቴ ፡ ደግነት ፡ ይሙላ
ራሴን ፡ ከመውደድ ፡ ነፃ ፡ አድርገኝ
አባት ፡ ሆይ  !
አሁን ፡ መንፈስህን ፡ ስጠኝ
ኢየሱስን ፡ ልምሰል