ጠፊዋን ፡ ዓለም ፡ ተለይቼ (Tefiwan Alem Teleyechie)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ጠፊዋን ፡ ዓለም ፡ ተለይቼ
ለዘለዓለም ፡ ተሰናብቼ
የሚሞተው ፡ ተለውጦ
የማይሞተውን ፡ ኢየሱስን ፡ ለብሶ

ከጌታ ፡ ጋር ፡ ልሆን ፡ እናፍቃለሁ
ዓለምና ፡ ሃሣቧን ፡ ትቻለሁ
ከላይ ፡ የሚመጣውን ፡ እጠብቃለሁ
በቅጽበት ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ እነጠቃለሁ

አዝ፦ ጠፊዋን ፡ ዓለም ፡ ተለይቼ
ለዘለዓለም ፡ ተሰናብቼ
የሚሞተው ፡ ተለውጦ
የማይሞተውን ፡ ኢየሱስን ፡ ለብሶ

በጉጉት ፡ ናፍቆት ፡ ፊቱን ፡ ሳይ
ኢየሱሴን ፡ ስገናኝ ፡ ከላይ ፡ በሰማይ
ፊቴን ፡ ሲመለከት ፡ እንባዬን ፡ ሲያይ
እየዳሰሰ ፡ ዓይኔን ፡ ያብሳል

አዝ፦ ጠፊዋን ፡ ዓለም ፡ ተለይቼ
ለዘለዓለም ፡ ተሰናብቼ
የሚሞተው ፡ ተለውጦ
የማይሞተውን ፡ ኢየሱስን ፡ ለብሶ

ጌታ ፡ መምጣቱን ፡ ያሳውጃል
በደጅ ፡ እንደቆመ ፡ ሕይወቴ ፡ ያውቃል
ቀኑ ፡ እንደደረሰ ፡ ተረድቼ
ተጨማሪ ፡ ዘይት ፡ ልሻ ፡ ተግቼ

አዝ፦ ጠፊዋን ፡ ዓለም ፡ ተለይቼ
ለዘለዓለም ፡ ተሰናብቼ
የሚሞተው ፡ ተለውጦ
የማይሞተውን ፡ ኢየሱስን ፡ ለብሶ