ጠቢብ ፡ በጥበቡ ፡ አይመካ (Tebib Betebebu Ayemeka)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

1. አመጻዬ ፡ ወደ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ወሰደችኝ
ውኃ ፡ በሌለው ፡ በረሃ ፡ አንከራተተችኝ
ለውድቀቴ ፡ ዕውቀት ፡ ትዕቢቴን ፡ አስተማረችኝ
እውነት ፡ ስትወቅሰኝ ፡ ጥበብ ፡ ስትገስጸኝ
ጥማት ፡ ሊያቃጥለኝ ፡ እልህ ፡ ሲታገለኝ
መንፈሱ ፡ ሲወቅሰኝ ፡ ጌታን ፡ አገኘሁኝ

አዝ፦ ጠቢብ ፡ በጥበቡ ፡ አይመካ
ኃያልም ፡ በኃይሉ ፡ አይመካ
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጽድቅንና ፡ ፍርድን
በምድር ፡ ላይ ፡ ማድረጉን ፡ ያወቀ
በጌታ ፡ ይመካ

2. ሠማያዊ ፡ ጥበብ ፡ ዐይንን ፡ እከፍታለች
ለሰነፎች ፡ ብልሃትን ፡ ታስተምራለች
ከምዝምዝ ፡ ወርቅና ፡ ከቀይ ፡ ዕንቁ ፡ እበልጣለች
አጥብቀህ ፡ ብትይዛት ፡ ብትፈላልጋት
ድምጽህን ፡ አንስተህ ፡ ጥበብን ፡ ብትጠራት
ያን ፡ ጊዜ ፡ ታውቃለህ ፡ እግዚአብሔርን ፡ መፍራት

አዝ፦ ጠቢብ ፡ በጥበቡ ፡ አይመካ
ኃያልም ፡ በኃይሉ ፡ አይመካ
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጽድቅንና ፡ ፍርድን
በምድር ፡ ላይ ፡ ማድረጉን ፡ ያወቀ
በጌታ ፡ ይመካ

3. የዚህች ፡ ዓለም ፡ መርማሪ ፡ ወዴት ፡ አለ
የዘመናት ፡ ጥያቄ ፡ ያቃለለ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ሊቁ ፡ ለእኛ ፡ የተሰቀለ
ከበረሃው ፡ መሃል ፡ ሕይወትን ፡ ያፈለቀ
የሰይጣንን ፡ ስልጣን ፡ መትቶ ፡ ያደቀቀ
ለእርሱ ፡ ስንሸነፍ ፡ ጥያቄ ፡ አለቀ

አዝ፦ ጠቢብ ፡ በጥበቡ ፡ አይመካ
ኃያልም ፡ በኃይሉ ፡ አይመካ
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጽድቅንና ፡ ፍርድን
በምድር ፡ ላይ ፡ ማድረጉን ፡ ያወቀ
በጌታ ፡ ይመካ