From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
ወደ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ወስዶ ፡ ማባበልን ፡ ያውቅበታል
አቤት ፡ ይሄ ፡ ግሩም ፡ ጌታ ፡ እንግዲህስ ፡ ምን ፡ ይባላል
ታሪኬን ፡ ሁሉ ፡ ለዋውጦ ፡ በክብር ፡ አልጋ ፡ ላይ ፡ አስቀምጦ
ያጌጠ ፡ ልብስ ፡ አለበሰኝ ፡ ቆሻሻዬን ፡ አወላልቆ
አዝ፦ ታሪኬን ፡ የለወጠልኝን
አዲስ ፡ ምዕራፍ ፡ የከፈተልኝን
ይህን ፡ ኢየሱሴን ፡ ላመስግነው
ከሰማይ ፡ ሆኖ ፡ አይቶኛል ፡ መዋረዴን ፡ ተመልክቷል
ምህረትን ፡ ስላገኘሁ ፡ ልሰግድለት ፡ ይገባኛል
ዘይቱን ፡ በላዬ ፡ ሲያፈስ ፡ ፊቴ ፡ እንደመብራት ፡ አበራ
ምድረ ፡ በዳዬ ፡ ለምልሟል ፡ የሳቀ ፡ ጠላቴም ፡ አፍሯል
አዝ፦ ታሪኬን ፡ የለወጠልኝን
አዲስ ፡ ምዕራፍ ፡ የከፈተልኝን
ይህን ፡ ኢየሱሴን ፡ ላመስግነው
ሞትን ፡ እንኳን ፡ እስከምመኝ ፡ የአመጻ ፡ ቀን ፡ በረታብኝ
ዛሬ ፡ ይሄ ፡ ሁሉ ፡ የለም ፡ የድል ፡ ጌታ ፡ ስሙ ፡ ይክበር
ከማህጸን ፡ ተሸክሞ ፡ እስከሽምግልና ፡ የሚያደርስ
ፍቅር ፡ የተሞላ ፡ አምላክ ፡ ድል ፡ የሰጠኝ ፡ እርሱ ፡ ይንገሥ
አዝ፦ ታሪኬን ፡ የለወጠልኝን
አዲስ ፡ ምዕራፍ ፡ የከፈተልኝን
ይህን ፡ ኢየሱሴን ፡ ላመስግነው
ለወገኖቼ ፡ ማፈሪያ ፡ ላዩኝ ፡ ሁሉ ፡ መሰበሪያ
ሆኜ ፡ እንዳልቀር ፡ አዘነልኝ ፡ ታሪኬን ፡ ለዋወጠልኝ
የእሱን ፡ ማዳን ፡ ያያችሁ ፡ ክብሩ ፡ እንደእኔ ፡ የበራላችሁ
ለስሙ ፡ ክብር ፡ ዘምሩ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ አመስግኑ
አዝ፦ ታሪኬን ፡ የለወጠልኝን
አዲስ ፡ ምዕራፍ ፡ የከፈተልኝን
ይህን ፡ ኢየሱሴን ፡ ላመስግነው
|