ታላቅ ፡ አምላክ ፡ አለኝ (Talaq Amlak Alegn)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ከክፉ ፡ ጠላት ፡ ጋራ ፡ ተናንቆ
ነፍሴን ፡ ከሲኦል ፡ ከሞት ፡ አፍ ፡ ነጥቆ
መራራ ፡ ሕይወቴን ፡ ጣፋጭ ፡ አድርጓል
የአንስሳ ፡ ኑሮዬን ፡ ለውጦታል

አዝ፦ ታላቅ ፡ አምላክ ፡ አለኝ
አመልከዋለሁ ፡ ዘለዓለም (፪x)
የክብር ፡ አምላክ ፡ አለኝ
አከብረዋለሁ ፡ ዘለዓለም (፪x)

ዘር ፡ ከሌለበት ፡ ፍሬን ፡ ያበቅላል
ደመና ፡ ሳይኖር ፡ ዝናብ ፡ ያዘንባል
ያለመድሃኒት ፡ መፈወስ ፡ ያውቃል
እንዴርሱ ፡ ያለ ፡ ከቶ ፡ የት ፡ ይገኛል

አዝ፦ ታላቅ ፡ አምላክ ፡ አለኝ
አመልከዋለሁ ፡ ዘለዓለም (፪x)
የክብር ፡ አምላክ ፡ አለኝ
አከብረዋለሁ ፡ ዘለዓለም (፪x)

ስሙ ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ኃይሉም ፡ ታላቅ ፡ ነው
ዙፋኑ ፡ ከጥንት ፡ ከዘለዓለም ፡ ነው
ድምጹም ፡ ሲያሰማት ፡ ነፍሴ ፡ ትዘላለች
የሰማይ ፡ ስልጣን ፡ ክብሩን ፡ እያየች

አዝ፦ ታላቅ ፡ አምላክ ፡ አለኝ
አመልከዋለሁ ፡ ዘለዓለም (፪x)
የክብር ፡ አምላክ ፡ አለኝ
አከብረዋለሁ ፡ ዝለዓለም (፪x)

ዓለማት ፡ ሲያልፉ ፡ ዘመናት ፡ ሁሉ
እርሱ ፡ ግን ፡ አለ ፡ ዛሬም ፡ በኃይሉ
ነገም ፡ ይኖራል ፡ ማን ፡ ይነካዋል
ተጠግቼውም ፡ እኔን ፡ አኩርቶኛል

አዝ፦ ታላቅ ፡ አምላክ ፡ አለኝ
አመልከዋለሁ ፡ ዘለዓለም (፪x)
የክብር ፡ አምላክ ፡ አለኝ
አከብረዋለሁ ፡ ዝለዓለም (፪x)