From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
የስቱን ፡ ጸባይ ፡ ነው ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ የቻልከው
እያባበልክ ፡ ይዘህ ፡ አንተ ፡ የምታኖረው
እውነትም ፡ ፍቅር ፡ ነህ ፡ ሌላ ፡ ማንም ፡ የለም
ደከመኝ ፡ ሰለቸኝ ፡ መረረኝ ፡ አትልም
አዝ፦ ታጋሽና ፡ ሩህሩህ ፡ አምላክ ፡ አንተ ፡ ነህ
እስከ ፡ ሺ ፡ ትውልድ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህ
አንዴና ፡ ሁለቴ ፡ አይተህ ፡ አትሰለችም
እንደየአመሉ ፡ ታቅፋለህ ፡ ሁሉንም
ሰው ፡ የሰለችንን ፡ ከአፉ ፡ የተፋንን
እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ ወዶ ፡ የሚያኖረን ፡ ስንቶች ፡ ነን
መልካም ፡ ሆነን ፡ አይደል ፡ የምንኖር ፡ በቤቱ
ስለበዛለን ፡ ነው ፡ የጌታ ፡ ምህረቱ
አዝ፦ ታጋሽና ፡ ሩህሩህ ፡ አምላክ ፡ አንተ ፡ ነህ
እስከ ፡ ሺ ፡ ትውልድ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህ
አንዴና ፡ ሁለቴ ፡ አይተህ ፡ አትሰለችም
እንደየአመሉ ፡ ታቅፋለህ ፡ ሁሉንም
አመሌ ፡ ጠማማ ፡ ከሰው ፡ የማይገጥም
በቀኝ ፡ ሲሉኝ ፡ ግራ ፡ ፍፁም ፡ አልመችም
አንተ ፡ ግን ፡ አጸለች ፡ እውነትም ፡ ፍቅር ፡ ነህ
ሁሌ ፡ በፈገግታ ፡ ትቀበለኛለህ
አዝ፦ ታጋሽና ፡ ሩህሩህ ፡ አምላክ ፡ አንተ ፡ ነህ
እስከ ፡ ሺ ፡ ትውልድ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህ
አንዴና ፡ ሁለቴ ፡ አይተህ ፡ አትሰለችም
እንደየአመሉ ፡ ታቅፋለህ ፡ ሁሉንም
የሰው ፡ ልብ ፡ ከሁሉ ፡ ይልቅ ፡ ተንኮለኛ
እጅግም ፡ ከፉ ፡ ነው ፡ መስሎ ፡ አመለኛ
ቢሆንም ፡ አትሰለች ፡ ተሸክመኸዋል
እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነህ ፡ ክብር ፡ ይገባሃል
አዝ፦ ታጋሽና ፡ ሩህሩህ ፡ አምላክ ፡ አንተ ፡ ነህ
እስከ ፡ ሺ ፡ ትውልድ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህ
አንዴና ፡ ሁለቴ ፡ አይተህ ፡ አትሰለችም
እንደየአመሉ ፡ ታቅፋለህ ፡ ሁሉንም
|