ስንት ፡ ብፅዕና ፡ ታደለ (Sint Bitsina Tadele)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ስንት ፡ ብፅዕና ፡ ታደለ?
ኢየሱስን ፡ ያገኘ
ከእርሱ ፡ የተዛመደው
ልቡ ፡ ሰላም ፡ አለው
ልናዳምጥ ፡ የእርሱን ፡ ቃል
ከሁሉ ፡ ይገዳል
ከምሕረቱ ፡ እንጥገብ
በእግሩ ፡ አጠገብ

ምን ፡ አለው ፡ ጌጥ ፡ ወርቅ ፡ ደስታ?
የሚበን ፡ አቧራ
ያመነ ፡ በኢየሱስ ፡ ግን
ያዘ ፡ ዕፁብ ፡ ሃብትን
ጤና ፣ ትርፍ ፣ ወዳጅ ፣ ሕይወት
ምንም ፡ ቢጠፋበት
ኢየሱስ ፡ ከእርሱ ፡ ይኖራል
ጉዳቱን ፡ ይተካል

ኢየሱስ ፡ ሆንህልኝ ፡ ጋሻ
ሠይፍ ፣ መዝገብ ፣ ትርፍ ፣ አምባ
በሌት ፡ ሆንህ ፡ ፀሐዬ
የማይክድ ፡ ወዳጄ
በውርጅብኝ ፡ ነህ ፡ ተገን
ማጽንያ ፡ በሃዘን
ኃይል ፡ በጭንቀት ፣ በድካም
በሞት ፡ ሕይወት ፣ ሰላም

ከኃጢአቴ ፡ አጥራኝ
ፅድቅን ፡ ፍጠርልኝ
አግባልኝ ፡ ቅዱስ ፡ ድፍረት
አድነኝ ፡ ከውድቀት
ሁን ፡ እረኛዬ ፡ ዘንጌ
አትራቅ ፡ ከእኔ
ከመቃብሬ ፡ አንሳኝ
በሰማያት ፡ አግባኝ