ሥሙ ፡ ይክበር ፡ ይንገሥ ፡ ጌታ (Simu Yikber Yinges Gieta)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ሳምንት ፡ ወራት ፡ ዐመታት ፡ ያልፋሉ
ሰማይ ፡ ምድር ፡ ይጠቀለላሉ
ሕያው ፡ ሆኖ ፡ ለሚኖረው
በአዲስ ፡ ቅኔ ፡ ክብር ፡ እንስጠው

አዝ ፣
ሥሙ ፡ ይክበር ፡ ይንገሥ ፡ ጌታ
የሞተልኝ ፡ በጐልጐታ
ዘምሩለት ፡ በአዲስ ፡ ቅኔ
ከፍ ፡ አድርጉት ፡ በጉባዔ

ባሕረ ፡ ኤርትራን ፡ በክንዱ ፡ የከፈለ
በደረቅ ፡ ምድር ፡ ያሳለፈ
ሕያው ፡ ሆኖ ፡ ለሚኖረው
በአዲስ ፡ መዝሙር ፡ ክብር ፡ እንስጠው

አዝ ፣
ሥሙ ፡ ይክበር ፡ ይንገሥ ፡ ጌታ
የሞተልኝ ፡ በጐልጐታ
ዘምሩለት ፡ በአዲስ ፡ ቅኔ
ከፍ ፡ አድርጉት ፡ በጉባዔ

ኅይሉ ፡ ግርማው ፡ ሞገሱ ፡ አስፈሪ
ለዘለዓለም ፡ በዙፋን ፡ ኗሪ
ሥልጣን ፡ ሁሉ ፡ የእርሱ ፡ ለሆነው
ከልባችን ፡ እንወድሰው

አዝ ፣
ሥሙ ፡ ይክበር ፡ ይንገሥ ፡ ጌታ
የሞተልኝ ፡ በጐልጐታ
ዘምሩለት ፡ በአዲስ ፡ ቅኔ
ከፍ ፡ አድርጉት ፡ በጉባዔ