ሲከፋኝ ፡ ወደ ፡ አምላኬ (Sikefagn Wede Amlakie)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ሲከፋኝ ፡ ወደ ፡ አምላኬ
እጮሃለሁ ፡ ተንበርክኬ
ረዳቴ ፡ እንደሆነ ፡ አውቃለሁ
ሕይወቴን ፡ ሰጥቼዋለሁ

አዝ፦ ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ማን ፡ አለኝ
ሕይወቴን ፡ የሚይዘኝ
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ እጄን ፡ ያዘኝ
ወደ ፡ ቤትህም ፡ አድርሰኝ

በክብርህ ፡ ከላይ ፡ ስትመጣ
ወይም ፡ ነፍሴ ፡ ስትወጣ
እፊትህ ፡ ቀርቤ ፡ አንተን ፡ ሳይ
እንደ ፡ ቃልህ ፡ ቆሜ ፡ ልታይ

አዝ፦ ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ማን ፡ አለኝ
ሕይወቴን ፡ የሚይዘኝ
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ እጄን ፡ ያዘኝ
ወደ ፡ ቤትህም ፡ አድርሰኝ

እንደ ፡ ቃልህ ፡ ተጠርቼ
መጥቻለሁ ፡ ሁሉን ፡ ትቼ
ቃልህ ፡ እንደሚያዘኝ ፡ ልሆን
አቅቶኛል ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ

አዝ፦ ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ማን ፡ አለኝ
ሕይወቴን ፡ የሚይዘኝ
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ እጄን ፡ ያዘኝ
ወደ ፡ ቤትህም ፡ አድርሰኝ