ሺህ ፡ ጊዜ ፡ ሺህ (Shih Gizie Shih)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

Al

<u>አዝ</u>፦ ሺህ ፡ ጊዜ ፡ ሺህ ፡ ኦሆሆ ፡ አሃሃ
እልፍ ፡ ጊዜ ፡ እልፍ ፡ ኦሆሆ ፡ አሃሃ (፪x)

ባመሰግንህ ፡ እኔ ፡ አልጠግብም ፡ ባመሰግንህ
ብዘምርልህ ፡ እኔ ፡ አልጠግብም ፡ ብዘምርልህ
ከፍ ፡ በል ፡ ብልህ ፡ እኔ ፡ አልጠግብም ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ብልህ
ዕልል ፡ ብልልህ ፡ እኔ ፡ አልጠግብም ፡ ዕልል ፡ ብልልህ

የናርዶስ ፡ ሽቶዬ ፡ ውዴ ፡ ኢየሱስ
ሽታህ ፡ ያውደኛል ፡ ይላል ፡ ደስ ፡ ደስ
የአፍህ ፡ ቃል ፡ ደግሞ ፡ ህግጋትህ
ጣፋጭ ፡ ሆኖልኛል ፡ እንደስምህ

<u>አዝ</u>፦ ባመሰግንህ ፡ እኔ ፡ አልጠግብም ፡ ባመሰግንህ
ብዘምርልህ ፡ እኔ ፡ አልጠግብም ፡ ብዘምርልህ
ከፍ ፡ በል ፡ ብልህ ፡ እኔ ፡ አልጠግብም ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ብልህ
ዕልል ፡ ብልልህ ፡ እኔ ፡ አልጠግብም ፡ ዕልል ፡ ብልልህ

ሺህ ፡ ጊዜ ፡ ሺህ ፡ ኦሆሆ ፡ አሃሃ
እልፍ ፡ ጊዜ ፡ እልፍ ፡ ኦሆሆ ፡ አሃሃ (፪x)

ሰንሰለቴን ፡ በጠስክ ፡ እስራቴን
በደምህ ፡ አጠብከው ፡ ኃጢአቴን
በቅዱስ ፡ መንፈስህ ፡ ቀደስከኝ
የመንግሥትህን ፡ ካህን ፡ አደረግኸኝ

<u>አዝ</u>፦ ባመሰግንህ ፡ እኔ ፡ አልጠግብም ፡ ባመሰግንህ
ብዘምርልህ ፡ እኔ ፡ አልጠግብም ፡ ብዘምርልህ
ከፍ ፡ በል ፡ ብልህ ፡ እኔ ፡ አልጠግብም ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ብልህ
ዕልል ፡ ብልልህ ፡ እኔ ፡ አልጠግብም ፡ ዕልል ፡ ብልልህ

ሺህ ፡ ጊዜ ፡ ሺህ ፡ ኦሆሆ ፡ አሃሃ
እልፍ ፡ ጊዜ ፡ እልፍ ፡ ኦሆሆ ፡ አሃሃ (፪x)

ክበር ፡ ብልህ ፡ ያንስብሃል
ንገሥ ፡ ብልህ ፡ ያንስብሃል (፬x)

አንደበቴን ፡ በፀጋህ ፡ አጣፍጠህ
ዓይኖችህን ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ አቅንተህ
በእጆችህ ፡ አቅፈኸኝ ፡ ደግፈህ
ምሥጋናዬን ፡ ሰማህ ፡ ጆሮህንም ፡ ከፍተህ

ክበር ፡ ብልህ ፡ ያንስብሃል
ንገሥ ፡ ብልህ ፡ ያንስብሃል (፬x)

አዘምራለሁ (፫x)
አዘምራለሁ (፫x)

አምላኬ ፡ በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ባርኮኛል
ኑሮዬን ፡ የእርሱ ፡ አድርጐ ፡ ወስዶኛል
ቃላት ፡ አጣሁኝ ፡ ምን ፡ እለዋለሁ
ያለኝ ፡ ይኼ ፡ ነው ፡ እዘምራለሁ

ዝማሬዬን ፡ ጌታ ፡ ከወደደው
እስኪ ፡ ልነሳና ፡ ላሞጋግሰው
አምልኮዬን ፡ ጌታ ፡ ከወደደው
እስቲ ፡ ልነሳና ፡ ላሞጋግሰው

አዘምራለሁ (፫x)
አዘምራለሁ (፫x)

በጠላት ፡ ግዛት ፡ ላይ ፡ ሥልጣኑን ፡ ሰጥቶኛል
አምላኬ ፡ በጠላቶቼ ፡ ላይ ፡ ሾሞኛል
ምሥጋና ፡ ላብዛ ፡ አከብረዋለሁ
ክብር ፡ የሚገባው ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው

ዝማሬዬን ፡ ጌታ ፡ ከወደደው
እስኪ ፡ ልነሳና ፡ ላሞጋግሰው
አምልኮዬን ፡ ጌታ ፡ ከወደደው
እስቲ ፡ ልነሳና ፡ ላሞጋግሰው