ሸክም ፡ ይሰማሃል ፡ ወይ (Shekem Yesemahal Woy)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ሸክም ፡ ይሰማሃል ፡ ወይ?
ክርስቲያን ፡ ወገኔ ፡ ሆይ
ለሚጠፉት ፡ ወገኖች ፡ ልብህ ፡ ያዝንብሃል ፡ ወይ?
ጥፋታቸው ፡ ተሰምቶህ ፡ አዝነህ ፡ ትፀልያለህ?
በራስህ ፡ ተመክተህ ፡ ወይስ ፡ በመፍረድ ፡ ላይ ፡ ነህ?

በሞት ፡ ጐዳና ፡ ላይ ፡ ሆነው ፡ ወደ ፡ ሞት ፡ ሲያዘግሙ
ልብህስ ፡ ያዝንብሃል ፡ ወይ?
ይሰማሃል ፡ ወይ ፡ ሸክሙ?

አዝ፦ ሸክም ፡ ይሰማሃል ፡ ወይ?
ክርስቲያን ፡ ወገኔ ፡ ሆይ
ለሚጠፉት ፡ ወገኖች ፡ ልብህ ፡ ያዝንብሃል ፡ ወይ?
ጥፋታቸው ፡ ተሰምቶህ ፡ አዝነህ ፡ ትፀልያለህ?
በራስህ ፡ ተመክተህ ፡ ወይስ ፡ በመፍረድ ፡ ላይ ፡ ነህ?

አንተስ ፡ በመጀመሪያ ፡ የት ፡ ነበርህ?
ከየት ፡ መጣህ?
በከንቱ ፡ ስትሮጥ ፡ ስትባዝን ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ያወጣህ

አዝ፦ ሸክም ፡ ይሰማሃል ፡ ወይ?
ክርስቲያን ፡ ወገኔ ፡ ሆይ
ለሚጠፉት ፡ ወገኖች ፡ ልብህ ፡ ያዝንብሃል ፡ ወይ?
ጥፋታቸው ፡ ተሰምቶህ ፡ አዝነህ ፡ ትፀልያለህ?
በራስህ ፡ ተመክተህ ፡ ወይስ ፡ በመፍረድ ፡ ላይ ፡ ነህ?

ጌታ ፡ እንደሞተላቸው ፡ ስለ ፡ እነርሱ ፡ ተጐድቶ
አንተ ፡ ዝም ፡ ካልክ
ወንድሜ ፡ ማን ፡ ይናገራል ፡ ከቶ?

አዝ፦ ሸክም ፡ ይሰማሃል ፡ ወይ?
ክርስቲያን ፡ ወገኔ ፡ ሆይ
ለሚጠፉት ፡ ወገኖች ፡ ልብህ ፡ ያዝንብሃል ፡ ወይ?
ጥፋታቸው ፡ ተሰምቶህ ፡ አዝነህ ፡ ትፀልያለህ?
በራስህ ፡ ተመክተህ ፡ ወይስ ፡ በመፍረድ ፡ ላይ ፡ ነህ?

ፍቅር ፡ የተሞላ ፡ መልዕክት ፡ ከፍቅር ፡ አምላክ ፡ ከላይ
ኢየሱስ ፡ እንደሚያድን
መናገር ፡ አትችልም ፡ ወይ?

አዝ፦ ሸክም ፡ ይሰማሃል ፡ ወይ?
ክርስቲያን ፡ ወገኔ ፡ ሆይ
ለሚጠፉት ፡ ወገኖች ፡ ልብህ ፡ ያዝንብሃል ፡ ወይ?
ጥፋታቸው ፡ ተሰምቶህ ፡ አዝነህ ፡ ትፀልያለህ?
በራስህ ፡ ተመክተህ ፡ ወይስ ፡ በመፍረድ ፡ ላይ ፡ ነህ?

ስለ ፡ ጌታ ፡ እንመስክር
እንናገር ፡ ስለ ፡ እርሱም
በመጨረሻውም ፡ ጊዜ ፡ ያለዋጋ ፡ አይተወንም

አዝ፦ ሸክም ፡ ይሰማሃል ፡ ወይ?
ክርስቲያን ፡ ወገኔ ፡ ሆይ
ለሚጠፉት ፡ ወገኖች ፡ ልብህ ፡ ያዝንብሃል ፡ ወይ?
ጥፋታቸው ፡ ተሰምቶህ ፡ አዝነህ ፡ ትፀልያለህ?
በራስህ ፡ ተመክተህ ፡ ወይስ ፡ በመፍረድ ፡ ላይ ፡ ነህ?