From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
ስትጨነቅ ፡ ሳለህ ፡ ጥራ ፡ ኢየሱስን
ከጥፋት ፡ ሁሉ ፡ ለመዳን
ያለህን ፡ ድካም ፡ ግለጽለት ፡ አሁን
ችግርህን ፡ ሁሉ ፡ ንገረው
በአዳኝ ፡ ፀጋው ፡ ያጠነክርሃል
ግን ፡ በአንተ ፡ ሥራ ፡ ፈጽመህ ፡ ሙተሃል
ስለዚህ ፡ ቶሎ ፡ ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ ቸኩል
የፀጋ ፡ ኃይሉን ፡ ተቀበል
አምላካችን ፡ ሃዘንን ፡ ሁሉ ፡ ያያል
የልብን ፡ ጩኸት ፡ ይሰማል
የሚያድስ ፡ ኃይልም ፡ ይሰድልሃል
በዕምነት ፡ ብቻ ፡ ተቀበል
አንተን ፡ ይወዳል
በፍቅሩም ፡ ይጠራል
የነፍስን ፡ ጥፋት ፡ ከቶ ፡ አልወደደም
ስለዚህ ፡ ኢየሱስን ፡ ሊሰዋ ፡ ላከው
በሞቱም ፡ ሁሉን ፡ አዳነ
ባጭሩ ፡ ዘመን ፡ የእንግድነት ፡ ኑሮህ
ጨለማ ፡ ብቻ ፡ የሞላ
ወደ ፡ ላይ ፡ አሻቅበህ ፡ ኢየሱስን ፡ እይ
ጨለማውንም ፡ ያጠፋል
ተስፋ ፡ አድርገው ፡
ለሁሉ ፡ ዘመንህ ፡ እርሱ ፡ ኃይልህ ፡ ነው
ከሞትህ ፡ ያዳነህ ፡ ብርሃኑ ፡ ይሠራል
በልብህ ፡ ገብቶ ፡ ዕውርነትህንም ፡ ያበራል
|