From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
ስንጓዝ ፡ በደረቅ ፡ አገር
ከዚህ ፡ ከሚጠፋ ፡ ዓለም
በዝማሬ ፡ እንሻገር
ወደ ፡ አዲስ ፡ የሩሣሌም
አዝ፦ እንደ ፡ ባሕር ፡ ሞገድ ፡ ጩኸት
ሰማያዊ ፡ መዝሙሩ ፡ ይደምቃል
ኃይል ፡ ምሥጋና ፡ ክብር ፡ ስግደት
ላምላክ ፡ በግ ፡ ይገባዋል
በዚህ ፡ ታች ፡ ለስደተኛ
ኃዘን ፡ መከራም ፡ ይበዛል
ግን ፡ ለጽዮን ፡ መንገደኛ
አክሊል ፡ ተዘጋጅቷል
አዝ፦ እንደ ፡ ባሕር ፡ ሞገድ ፡ ጩኸት
ሰማያዊ ፡ መዝሙሩ ፡ ይደምቃል
ኃይል ፡ ምሥጋና ፡ ክብር ፡ ስግደት
ላምላክ ፡ በግ ፡ ይገባዋል
እሥራኤል ፡ በባቤል ፡ ወንዞች
እያለቀሱ ፡ ሲኖሩ
የየሩሣሌም ፡ ደጆች
ሁሉ ፡ ቀን ፡ ተዘከሩ
አዝ፦ እንደ ፡ ባሕር ፡ ሞገድ ፡ ጩኸት
ሰማያዊ ፡ መዝሙሩ ፡ ይደምቃል
ኃይል ፡ ምሥጋና ፡ ክብር ፡ ስግደት
ላምላክ ፡ በግ ፡ ይገባዋል
የሰማይ ፡ ወራሾች ፡ ሁሉ
በዚህ ፡ ታች ፡ እንዳትቀሩ
ባምላክ ፡ ኃይል ፡ በጽኑ ፡ ቃሉ
ሁል ፡ ጊዜ ፡ ተዳፈሩ
አዝ፦ እንደ ፡ ባሕር ፡ ሞገድ ፡ ጩኸት
ሰማያዊ ፡ መዝሙሩ ፡ ይደምቃል
ኃይል ፡ ምሥጋና ፡ ክብር ፡ ስግደት
ላምላክ ፡ በግ ፡ ይገባዋል
|