ሥሙ ፡ ይክበርልን (Semu Yekberelen)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ሥሙ ፡ ይክበርልን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
የሰው ፡ ልጅ ፡ ፈጣሪ ፡ የአለም ፡ ንጉሥ (፪x)
ስሙን ፡ እንጠራለን ፡ በዕልልታ
አናፍርም ፡ በኢየሱስ ፡ በእኛ ፡ ጌታ

አንደበት ፡ ተከፍቶ ፡ በየዕለቱ
ፈጣሪውን ፡ ያክብር ፡ በዕውነቱ
የዓለም ፡ ጥበብ ፡ ጠፍቶ ፡ ከውስጣችን
ኢየሱስ ፡ ይክበር ፡ በሥጋችን

አዝ፦ ሥሙ ፡ ይክበርልን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
የሰው ፡ ልጅ ፡ ፈጣሪ ፡ የአለም ፡ ንጉሥ (፪x)
ስሙን ፡ እንጠራለን ፡ በዕልልታ
አናፍርም ፡ በኢየሱስ ፡ በእኛ ፡ ጌታ

በወንጌል ፡ አናፍርም ፡ ኃይላችን ፡ ነው
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሥሙ ፡ መጠጊያ ፡ ነው
ስሙን ፡ እንጠራለን ፡ በአንድ ፡ ላይ
ኃያል ፡ ነው ፡ ጌታችን ፡ በዓለም ፡ ላይ

አዝ፦ ሥሙ ፡ ይክበርልን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
የሰው ፡ ልጅ ፡ ፈጣሪ ፡ የአለም ፡ ንጉሥ (፪x)
ስሙን ፡ እንጠራለን ፡ በዕልልታ
አናፍርም ፡ በኢየሱስ ፡ በእኛ ፡ ጌታ

አይገደንም ፡ ለእኛ ፡ በዕውነቱ
ሰይጣንም ፡ ቢዋጋ ፡ በየዕለቱ
ያመንነውን ፡ ይዘን ፡ እንጸናለን
ኃይልን ፡ በሚሰጠን ፡ እንቆማለን

አዝ፦ ሥሙ ፡ ይክበርልን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
የሰው ፡ ልጅ ፡ ፈጣሪ ፡ የአለም ፡ ንጉሥ (፪x)
ስሙን ፡ እንጠራለን ፡ በዕልልታ
አናፍርም ፡ በኢየሱስ ፡ በእኛ ፡ ጌታ