ስሜ ፡ በተጠራ ፡ ጊዜ (Semie Betetera Gizie)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝስሜ ፡ በተጠራ ፡ ጊዜ (፫x)
ስሜ ፡ ሲጠራ ፡ እገኛለሁ ፡ እዚያ

የጌታ ፡ መለከት ፡ ሲነፋ ፡ ጊዜውም ፡ ሲፈጸም
ክርስቶስ ፡ በክብር ፡ ይገለጣል ፡ ዳግም
ሓጣን ፡ ከፊቱ ፡ ይጠፋሉ ፡ እንደትቢያ
ስሜ ፡ ሲጠራ ፡ እሆናለሁ ፡ እዚያ

አዝስሜ ፡ በተጠራ ፡ ጊዜ (፫x)
ስሜ ፡ ሲጠራ ፡ እገኛለሁ ፡ እዚያ

ጭጋግ ፡ በሌለው ፡ ጧት
በጌታ ፡ የሞቱ ፡ ሲነሱ
ይላቸዋል ፡ ቅዱሳኔ ፡ ይቀደሱ
አእላፋት ፡ መላእክት ፡ ይከቡታል ፡ በዙሪያ
ስሜ ፡ ሲጠራ ፡ እገኛለሁ ፡ እዚያ

አዝስሜ ፡ በተጠራ ፡ ጊዜ (፫x)
ስሜ ፡ ሲጠራ ፡ እገኛለሁ ፡ እዚያ

መንጋህ ፡ ነን ፡ አስበን
ጠላታችን ፡ እንዳይከበን
ጠብቀን ፡ እንደክቡር ፡ እይንህ ፡ ብሌን
አንተ ፡ ጠርተህ ፡ ቀስቅሰኝ
ቆሜ ፡ እንድገኝ ፡ ከዚያ
ስሜ ፡ ሲጠራ ፡ እገኛለሁ ፡ ከዚያ

አዝስሜ ፡ በተጠራ ፡ ጊዜ (፫x)
ስሜ ፡ ሲጠራ ፡ እገኛለሁ ፡ እዚያ