ስመለከት ፡ ያን ፡ ድንቅ ፡ መስቀል (Semeleket Yan Denq Mesqel)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ስመለከት ፡ ያን ፡ ድንቅ ፡ መስቀል
መድህኔ ፡ የሞተበትን
እንቀዋለሁ ፡ ሕይወቴን
ትምክህቴም ፡ ከንቱ ፡ ይሆናል

ከቅዱስ ፡ መስቀልህ ፡ በቀር
እንዳልመካ ፡ ከልክል ፡ ጌታ
ስራዬን ፡ ጥዬ ፡ በአንተ ፡ እግር
እሰግዳለሁ ፡ በጐልጐታ

እይ ፡ ከራሱ ፡ ከእጁ ፡ ከእግሩም
የከበረ ፡ ደሙ ፡ ፈሶአል
እንዴት ፡ ያለ ፡ ፍቅር ፡ ሆኖአል
የሚሸከም ፡ የእኔን ፡ መርገም

ዓለምን ፡ ሁሉ ፡ ብሰጥህ
ያንስብህ ፡ ነበር ፡ ስጦታህ
ሕይወቴንና ፡ ነፍሴን ፡ ይኸው
ተቀበለኝ ፡ ሳቀርብልህ