ሠልፉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው (Selfu Yegziabhier New)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ሠልፉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው
ውጊያው ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው
ድሉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው
ባሪያው ፡ ምሥክር ፡ ነው

እግዚአብሔር ፡ ብርሃኔና ፡ መድኃኒቴ ፡ ነው
የሚያስፈርኝ ፡ ማነው?
እግዚአብሔር ፡ ለሕይወቴ ፡ መታመኛዋ ፡ ነው
አስደንጋጬ ፡ ማነው?
ክፉዎች ፡ አስጨንቂዎቼ
የነፍሴ ፡ ብርቱ ፡ ጠልቅቶቼ
ተሰነካክለው ፡ በጽኑ ፡ ወደቁ
በጌታ ፡ በኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ደቀቁ!

አዝ፦ ሠልፉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው
ውጊያው ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው
ድሉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው
ባሪያው ፡ ምሥክር ፡ ነው

ሠራዊት ፡ ቢሰፍርብኝ ፡ ልቤ ፡ አይፈራም
ሠልፍን ፡ ቢያስገመግም
እግዚአብሔርን ፡ አንዲት ፡ ነገር ፡ ለምኜዋለሁ
እርሷን ፡ እጠብቃለሁ
በሕይወቴ ፡ ዘመናት ፡ በሙሉ
በቤቱ ፡ ኖሬ ፡ እንደ ፡ ቃሉ
ጌታዬ ፡ ደስ ፡ ያለውን ፡ ሲሠራ
አይቼ ፡ ስለ ፡ ክብሩ ፡ ላወራ

አዝ፦ ሠልፉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው
ውጊያው ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው
ድሉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው
ባሪያው ፡ ምሥክር ፡ ነው

በመከራዬ ፡ ቀን ፡ በድንኳኑ ፡ ሠውሮኛል
በዓለቱ ፡ አጽንቶኛል
ዙሪያዬን ፡ ባሉ ፡ ጠላቶቼ ፡ ፊት ፡ አቆመኝ
ከፍ ፡ ከፍ ፡ አደረገኝ
አባቴና ፡ እናቴም ፡ ሲተውኝ
እግዚአብሔር ፡ ወዶ ፡ ተቀበለኝ
የዕልልታ ፡ መሥዋዕት ፡ እሠዋለሁ
ለአምላኬ ፡ ክብር ፡ እዘምራለሁ

አዝ፦ ሠልፉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው
ውጊያው ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው
ድሉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው
ባሪያው ፡ ምሥክር ፡ ነው