ስለብዙ ፡ ምህረትህ ፡ ቸርነትህ (Sele Bezu Mehereteh Chereneteh)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

የምህረትህ ፡ ብዛቱ ፡ የቸርነትህ ፡ ጥልቀቱ
ከአዕምሮአችን ፡ በላይ ፡ ነው ፡ እንተ ፡ ለእኛ ፡ የሆንከው
የሕይወትን ፡ ቃል ፡ ሰጥተኸን ፡ በብዙ ፡ ተስፋ ፡ ሞልተኸን
ስንዝል ፡ እያበረታኸን ፡ ምህረትህ ፡ ዛሬም ፡ አቆመን

አዝ፦ ስለ ፡ ብዙ ፡ ምህረትህ ፡ ቸርነትህ
ብዙ ፡ ምሥጋና ፡ ክብር ፡ ላንተ ፡ ይድረስህ
መከናወንን ፡ ሰጥተኸናልና
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ላንተ ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና
ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ላንተ ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና

ከእሴይ ፡ ግንድ ፡ የወጣው ፡ በትር ፡ አመላለሰን ፡ በክብር
ዮርዳኖስንም ፡ ከፍለው ፡ አለቱንም ፡ ሰነጠቀው
ጠላታችንም ፡ አፈረ ፡ በትሩም ፡ እጅግ ፡ ከበረ
እኛም ፡ ከውድቀት ፡ ተነሳን ፡ ለመንግሥቱ ፡ ሰማይ ፡ በቃን

አዝ፦ ስለ ፡ ብዙ ፡ ምህረትህ ፡ ቸርነትህ
ብዙ ፡ ምሥጋና ፡ ክብር ፡ ላንተ ፡ ይድረስህ
መከናወንን ፡ ሰጥተኸናልና
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ላንተ ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና
ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ላንተ ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና

የተንተራስነው ፡ አለትህ ፡ መች ፡ ቆረቆረን ፡ ሌሊት
ውኃ ወጣ ፡ እንጂ ፡ ከእርሱ ፡ ስለ ፡ አሰበን ፡ ንጉሡ
ምድረ ፡ በዳውን ፡ አልፈናል ፡ ጌታ ፡ ድጋፍ ፡ ሆኖልናል
ስለበዛልን ፡ ምህረቱ ፡ ምሥጋና ፡ ይብዛ ፡ በቤቱ

አዝ፦ ስለ ፡ ብዙ ፡ ምህረትህ ፡ ቸርነትህ
ብዙ ፡ ምሥጋና ፡ ክብር ፡ ላንተ ፡ ይድረስህ
መከናወንን ፡ ሰጥተኸናልና
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ላንተ ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና
ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ላንተ ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና