ሰላም ፡ አለኝ ፡ ሰላም ፡ አለኝ (Selam Alegn Selam Alegn)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ሰላም ፡ አለኝ ፡ ሰላም ፡ አለኝ
ሰላም ፡ አለኝ ፡ በልቤ ፡ በልቤ
ቅዱስ ፡ ቃሉን ፡ አንብቤ
ደኅንነት ፡ አግኝቻለሁ
ስሞት ፡ ወደ ፡ ጌታ ፡ እሄዳለሁ

በኢየሱስ ፡ ደም ፡ በኢየሱስ ፡ ደም
ታጠበልኝ ፡ ኃጢአቴ ፡ ኃጢአቴ
ተለወጠ ፡ ሕይወቴ ፡ በወንጌል ፡ እጸናለሁ
ስሞት ፡ ወደ ፡ ጌታ ፡ እሄዳለሁ

ዕረፍት ፡ አለኝ ፡ ዕረፍት ፡ አለኝ
ዕረፍት ፡ አለኝ ፡ በኢየሱስ ፡ በኢየሱስ
የማይጠፋ ፡ ደስታ ፡ የማይናወጥ ፡ ተስፋ
በሕይወቴ ፡ በጣም ፡ ተስፋፋ

ተለወጥኩኝ ፡ ተለወጥኩኝ
ተለወጥኩኝ ፡ በኢየሱስ ፡ በኢየሱስ
አዲስ ፡ ፍጥረት ፡ ሆኛለሁ ፡ መንፈሱን ፡ አግኝቻለሁ
ስሞት ፡ ወደ ፡ ጌታ ፡ እሄዳለሁ

ሃዘን ፡ የለም ፡ ጭንቀት ፡ የለም
ፍርሃት ፡ ጠፍቷል ፡ ከልቤ ፡ ከልቤ
መንፈሱ ፡ ያጽናናኛል ፡ በደስታ ፡ ሞልቶኛል
ጌታ ፡ ዘወትር ፡ ይጠብቀኛል

ላመስግነው ፡ ላመስግነው
ላመስግነው ፡ ጌታዬን ፡ ጌታዬን
በመስቀል ፡ ተሰቃይቶ ፡ ከፈለልኝ ፡ ዕዳዬን
ክብር ፡ ክብር ፡ ለሥሙ ፡ ይሁን