ስላደረክልን ፡ እናቅርብ (Seladerekelen Enaqreb)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝስላደረክልን ፡ እናቅርብ ፡ ምሥጋና (፪x)
ምህረትህ ፡ ለልጅ ፡ ልጅ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አላለቅምና

አንመሰክራለን ፡ ታማኝ ፡ ነህ ፡ ጌታችን
ውለታ ፡ አድርገሃል ፡ ለቤተሰባችን
እኛም ፡ እንዳናፍር ፡ ስምህን ፡ አከብረሃል
u>ታማኝ (፪x) ፡ መሆንህን ፡ ጌታ ፡ መስክረሃል

አዝስላደረክልን ፡ እናቅርብ ፡ ምሥጋና (፪x)
ምህረትህ ፡ ለልጅ ፡ ልጅ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አላለቅምና

በቃልህ ፡ ተስፋ ፡ ላይ ፡ ልክ ፡ እንደተጻፈው
የልባችንን ፡ መሻት ፡ በሙሉ ፡ ፈጸምከው
ከአርያም ፡ ደርሶ ፡ የለመንንህ ፡ ሁሉ
ለእኛ (፪x) ፡ ስላደረከው ፡ ሰዎች ፡ ዕልል ፡ አሉ

አዝስላደረክልን ፡ እናቅርብ ፡ ምሥጋና (፪x)
ምህረትህ ፡ ለልጅ ፡ ልጅ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አላለቅምና

እንወድሻለን ፡ በቅኔና ፡ በመዝሙር
ስለገለጽክልን ፡ ሰማያዊ ፡ ፍቅር
ስለዚህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በሰዎች ፡ ፊት ፡ ቆምን
ላንተ ፡ ለስምህ ፡ ምጋና ፡ እንዘምራለን

አዝስላደረክልን ፡ እናቅርብ ፡ ምሥጋና (፪x)
ምህረትህ ፡ ለልጅ ፡ ልጅ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አላለቅምና

እንመሰክራለን ፡ አናፍርም ፡ ሁልጊዜ
አውጥተኸናልና ፡ ከመንፈስ ፡ ትካዜ
በለቅሶአችን ፡ ፈንታ ፡ ሰጥተኸናል ፡ ደስታ
ክብር (፪x) ፡ ይሁን ፡ ለአንተ ፡ የሠራዊት ፡ ጌታ

አዝስላደረክልን ፡ እናቅርብ ፡ ምሥጋና (፪x)
ምህረትህ ፡ ለልጅ ፡ ልጅ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አላለቅምና