From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
ሳይመለስ ፡ ይዘገያል
ሰማያዊ ፡ ጌታ
ሙሽራዪቱ ፡ በውርደት
ትኖራለች ፡ ገና
ክቡር ፡ የበዓል ፡ ልብስ ፡ አጣች
ዕንቆቹ ፡ ጠፉባት
የሞቀ ፡ የጥንት ፡ ፍቅር
አሁን ፡ ቀዘቀዛት
የአምላክ ፡ ቤት ፡ ተጐዳ
ሰላሙ ፡ ጠፋበት
ልጆች ፡ ይቀየማሉ
ሲጓዙ ፡ ባንድነት
ደፋሮች ፡ ይክዳሉ
ያን ፡ ቅዱስ ፡ ክብር ፡ ስም
ያረምጣል ፡ በሰዎች
የጠብ ፡ የክፋት ፡ ፍም
እንደ ፡ ነጣቂ ፡ ንሥር
ሲረብብ ፡ በሰማይ
ኃጥአን ፡ ያንዣብባሉ
በክርስቶስ ፡ ማኅበር ፡ ላይ
ፈራጁ ፡ ቀረበባት
በጽድቅ ፡ ሊቀሥፋት
የፀጋን ፡ ዘመን ፡ ናቀች
በፍቅሩ ፡ ሲጠራት
እላንት ፡ አሕዛብ ፡ ተነሡ
ለማኅበሩ ፡ ሃፍረት
በመስቀል ፡ ተከማቹ
ልታገኙ ፡ ሕይወት
በዕምነት ፡ በረታችሁ
ፍቅራችሁን ፡ ግለጡ
ሕዝብ ፡ ወንጌልን ፡ ሲቀበል
ከፍ ፡ እንዲል ፡ አሳዩ
ዕንቅልፍ ፡ የወደቀባት
ሙሽራይቱ ፡ ትንቃ
ከፍርድ ፡ ነፃ ፡ ያወጣ
ድንቅ ፡ ተስፋውን ፡ ትስማ
ለጠፉበት ፡ ልጆቹ
አምላክ ፡ እንዲራራ
በብርሃን ፡ እንዲመራ
አማኝ ፡ ሁሉ ፡ ያውራ
እንዲህ ፡ ሲሆን ፡ ጌታችን
በፍጥነት ፡ ይመጣል
ሙሽራይቱን ፡ ከውርደት
ለክብረት ፡ ያስነሣል
እሥራዔል ፡ ሲሰበሰብ
ለክርስቶስ ፡ በዕምነት
ሊሆን ፡ ለራሱ ፡ ደስታ
ለዓለም ፡ በረከት
|