ሳበን ፡ ሳበን ፡ ሳበን (Saben Saben Saben)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

እረግረጉን ፡ ለማለፍ ፡ ብርታት ፡ አግኝተን
በድጡ ፡ ላይ ፡ ለመሮጥ ፡ ፀጋህ ፡ ይብዛልን
መንፈስህ ፡ ካላቆመን ፡ ሥጋችን ፡ አልቻለም
አቅማችንን ፡ አውቀናል ፡ ሕይወት ፡ ዋዛ ፡ አይደለም

አዝሳበን ፡ ሳበን ፡ ሳበን (፪x)
ሳበን ፡ በፀጋህ ፡ ሳበን ፡ በኃይልህ
ከአንተ ፡ ኋላ ፡ እንሮጣለን
ሳበን ፡ ሳበን ፡ ሳበን (፪x)

እንቅፋቱ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ የሚገዳደረን
ከፊታችን ፡ የሚቆም ፡ ሊያሰናክለን
ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ በፀጋህ ፡ አንተ ፡ ከሳብከን
እሩጫችንን ፡ በድል ፡ እንፈጽማለን

አዝሳበን ፡ ሳበን ፡ ሳበን (፪x)
ሳበን ፡ በፀጋህ ፡ ሳበን ፡ በኃይልህ
ከአንተ ፡ ኋላ ፡ እንሮጣለን
ሳበን ፡ ሳበን ፡ ሳበን (፪x)

በፍቅር ፡ ሰንሰለት ፡ በታሰርንበት ፡ ላይ
ድርብ ፡ ፀጋህ ፡ ይጨመር ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ
ልንሮጥ ፡ በስተኋላህ ፡ ላንቆም ፡ ላንለይህ
ጌታ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ሆይ ፡ አበርታን ፡ እባክህ

አዝሳበን ፡ ሳበን ፡ ሳበን (፪x)
ሳበን ፡ በፀጋህ ፡ ሳበን ፡ በኃይልህ
ከአንተ ፡ ኋላ ፡ እንሮጣለን
ሳበን ፡ ሳበን ፡ ሳበን (፪x)

ከሥጋ ፡ ደስታ ፡ ይልቅ ፡ ፍቅርህን ፡ አስበን
የወይናችንን ፡ ቦታ ፡ በትጋት ፡ ጠብቀን
ኋላችንን ፡ ኧረስተን ፡ ከኋላህ ፡ እሮጥን
ከእጣ ፡ ክፍላችን ፡ ላይ ፡ ሄደን ፡ እንቆማለን

አዝሳበን ፡ ሳበን ፡ ሳበን (፪x)
ሳበን ፡ በፀጋህ ፡ ሳበን ፡ በኃይልህ
ከአንተ ፡ ኋላ ፡ እንሮጣለን
ሳበን ፡ ሳበን ፡ ሳበን (፪x)