From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
በማልፍበት ፡ መንገድ ፡ በሕይወት ፡ ጐዳና
በየለት ፡ ውሎዬ ፡ ሳልፍ ፡ በጐንበስ ፡ ቀና
ሊገቡኝ ፡ አልቻሉም ፡ ለምን? ፡ ከዛስ ፡ እንዴት?
ለማ ፡ መች ፡ በማ ፡ ቀጣዩስ ፡ ወዴት?
በዚ ፡ ሁሉ ፡ ነፍሴ ፡ ስትጨነቅ
ያረጋጋል ፡ አንድ ፡ ነገርን ፡ ማወቅ
ሉዓላዊ ፡ ብቻህን ፡ ሉዓላዊ ፡ ነህ
ሉዓላዊ ፡ እግዚአብሔር ፡ሉዓላዊ ፡ ነህ
ሉዓላዊ ፡ ለምን ፡ እንዲ ፡ አደረክ ፡ አንተ ፡ አትባልም
ሉዓላዊ ፡ አንተን ፡ ደርሶ ፡ ሚጠይቅ ፡ የለም
ሸማኔ ፡ አንተ ፡ የሕይወቴ ፡ሸማኔ
ሸማኔ ፡ አንተ ፡ የሕይወቴ ፡ሸማኔ
ሸክላ ፡ ሰሪ ፡ አንተ ፡ የሕይወቴ ፡ ሸክላ ፡ ሰሪ
ሸክላ ፡ ሰሪ ፡ አንተ ፡ የሕይወቴ ፡ ሸክላ ፡ ሰሪ
ፈረዱ ፡ ሊረዱ ፡ የወደዱ
አሰቡ ፡ ምክንያት ፡ ሰበሰቡ
ዝም ፡ አልኩኝ
እንዳሉኝ ፡ ሆንኩኝ
ለበጐ ፡ ነው ፡ ቢሉኝ ፡ አሜን ፡ ብዬ ፡ ጮህኩኝ
አጥፍተሃል ፡ ቢሉኝ ፡ ማረኝ ፡ማረኝ ፡ አልኩኝ
ጠላት ፡ ነው ፡ ያሉኝ ፡ ለት ፡ ቆምኩኝ ፡ ለጦርነት
የሰው ፡ ክፋት ፡ ጠቆሙኝ ፡ አድነኝ ፡ አልኩኝ
ሊሰራህ ፡ ነው ፡ ታገስ ፡ እሺ ፡ አልኩኝ ፡ ጥርሴን ፡ ነከስኩኝ
እምነቴን ፡ አበረታሁ ፡ ቆምኩኝ ፡ በረታው ፡ ፀናሁኝ
አንዳንዴ ፡ ሕይወት ፡ እንዲ ፡ ነው
መልሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ ነው
ቢገባኝም ፡ ባይገባኝም
በኔ ፡ ሕይወት ፡ ሉዓላዊ ፡ ነው
ሉዓላዊ ፡ ብቻህን ፡ ሉዓላዊ ፡ ነህ
ሉዓላዊ ፡ እግዚአብሔር ፡ሉዓላዊ ፡ ነህ
ሉዓላዊ ፡ ለምን ፡ እንዲ ፡ አደረክ ፡ አንተ ፡ አትባልም
ሉዓላዊ ፡ አንተን ፡ ደርሶ ፡ ሚጠይቅ ፡ የለም
|