ርስቴ ፡ ተዋበችልኝ (Restie Tewabechelegn)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ርስቴ ፡ ተዋበችልኝ
ገመድ ፡ ባማረ ፡ ስፍራ ፡ ወደቀችልኝ
የርስቴ ፡ ገመድ ፡ ባማረ ፡ ስፍራ
ስለወደቀች ፡ ምንም ፡ አልፈራ

እግዚአብሔር ፡ የርስቴ ፡ ዕድል ፡ ፈንታ ፡ ነው
ርስቴን ፡ የሚያስውብ ፡ የሚያሰማምረው
በምድር ፡ ብጨነቅ ፡ ኑሮም ፡ ቢመረኝ
የሰማይ ፡ ርስቴን ፡ አሳመረልኝ

አዝ፦ ርስቴ ፡ ተዋበችልኝ
ገመድ ፡ ባማረ ፡ ስፍራ ፡ ወደቀችልኝ
የርስቴ ፡ ገመድ ፡ ባማረ ፡ ስፍራ
ስለወደቀች ፡ ምንም ፡ አልፈራ

የሕይወትን ፡ መንገድ ፡ ጌታዬ ፡ አሳየኝ
በሰማይ ፡ ርስት ፡ ተመራ ፡ አለኝ
በምድር ፡ ብጨነቅ ፡ ኑሮ ፡ ቢመረኝ
የሰማይ ፡ ርስቴን ፡ ውብ ፡ አረገልኝ

አዝ፦ ርስቴ ፡ ተዋበችልኝ
ገመድ ፡ ባማረ ፡ ስፍራ ፡ ወደቀችልኝ
የርስቴ ፡ ገመድ ፡ ባማረ ፡ ስፍራ
ስለወደቀች ፡ ምንም ፡ አልፈራ

ፍንድቅድቅ ፡ አለች ፡ ፈካች ፡ ሕይወቴ
ስለተዋበችልኝ ፡ ርስቴ
በምድር ፡ ብጨነቅ ፡ ኑሮም ፡ ቢመረኝ
የሰማይ ፡ ርስቴን ፡ ጌታ ፡ አስጌጠልኝ

አዝ፦ ርስቴ ፡ ተዋበችልኝ
ገመድ ፡ ባማረ ፡ ስፍራ ፡ ወደቀችልኝ
የርስቴ ፡ ገመድ ፡ ባማረ ፡ ስፍራ
ስለወደቀች ፡ ምንም ፡ አልፈራ