ርስትህን ፡ ለማላገጫ (Restehen Lemalagecha)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

በደልን ፡ ይቅር ፡ የሚል ፡ አመጻን ፡ የሚያሳልፍ
ከጥፋት ፡ ሊያድናቸው ፡ በርስቱ ፡ ላይ ፡ የሚፈርድ
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ አምላክ ፡ ማን ፡ ነው ፡ ምህረቱ ፡ የበዛ
ቅዱሳን ፡ ሲሰደዱ ፡ መከራም ፡ ሲበዛ

አዝ፦ ርስትህን ፡ ለማላገጫ ፡ አሳልፈህ ፡ አትስጥ
የተቀደሰ ፡ መቅደስህን ፡ በጠላት ፡ አታስረግጥ

የእግዚአብሔር ፡ ዕድል ፡ ፈንታ ፡ ተጽፏል ፡ ህዝቡ ፡ ነው
ሊሚያመልከው ፡ ሊያገለግለው ፡ ከግብጽ ፡ አገር ፡ ያፈለሰው
አርነቱን ፡ በባርነት ፡ ሊተካ ፡ የሚከጅለው
ይገባኛል ፡ የሚል ፡ ማን ፡ ነው? ፡ ርስቱ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው

አዝ፦ ርስትህን ፡ ለማላገጫ ፡ አሳልፈህ ፡ አትስጥ
የተቀደሰ ፡ መቅደስህን ፡ በጠላት ፡ አታስረግጥ

እስከዛሬ ፡ ከብረሃል ፡ በአህዛብ ፡ ተፈርተሃል
የጠላትን ፡ እርግማን ፡ በረከት ፡ አድርገሃል
የአሳዳጆችን ፡ ፈረሶች ፡ በባሕር ፡ አስጥመሃል
በክንድህ ፡ ተከላክለህ ፡ ርስትህን ፡ ጠብቀሃል

አዝ፦ ርስትህን ፡ ለማላገጫ ፡ አሳልፈህ ፡ አትስጥ
የተቀደሰ ፡ መቅደስህን ፡ በጠላት ፡ አታስረግጥ