ረዳት ፡ ያሻኛል ፡ የሚያቆመኝ (Redat Yashagnal Yemiyaqomegn)
From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ፦ ረዳት ፡ ያሻኛል ፡ የሚያቆመኝ
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ሆይ ፡ ና ፡ ደግፈኝ
አንተ ፡ ነህና ፡ ፅኑ ፡ ጉልበቴ
ጠላት ፡ ሲመጣ ፡ ፊት ፡ ለፊቴ
በእራሴ ፡ ጥሬ ፡ ኃይልን ፡ ሳጣ
ኃጢአት ፡ ሊውጠኝ ፡ ሲቃጣ
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ሆይ ፡ ደርሰህ ፡ እርዳኝ
ኃይልህ ፡ መንጥቆ ፡ ያውጣኝ
አዝ፦ ረዳት ፡ ያሻኛል ፡ የሚያቆመኝ
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ሆይ ፡ ና ፡ ደግፈኝ
አንተ ፡ ነህና ፡ ፅኑ ፡ ጉልበቴ
ጠላት ፡ ሲመጣ ፡ ፊት ፡ ለፊቴ
ሥጋዬ ፡ ምቾት ፡ ሲሰማው
ተመኝቶ ፡ ኃጢአት ፡ ሲያምረው
እንዳልወድቅ ፡ እኔ ፡ ተደልዬ
ኃይልን ፡ ሰጠኝ ፡ ጌታዬ
አዝ፦ ረዳት ፡ ያሻኛል ፡ የሚያቆመኝ
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ሆይ ፡ ና ፡ ደግፈኝ
አንተ ፡ ነህና ፡ ፅኑ ፡ ጉልበቴ
ጠላት ፡ ሲመጣ ፡ ፊት ፡ ለፊቴ
የእራሴ ፡ ጥረት ፡ አውቆ ፡ ሲከዳኝ
ጉዞው ፡ ከብዶብኝ ፡ ሲያቅተኝ
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ሆይ ፡ አበርታ ፡ ጉልበቴን
ድል ፡ ስጠኝ ፡ ልርታ ፡ ጠላቴን
አዝ፦ ረዳት ፡ ያሻኛል ፡ የሚያቆመኝ
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ሆይ ፡ ና ፡ ደግፈኝ
አንተ ፡ ነህና ፡ ፅኑ ፡ ጉልበቴ
ጠላት ፡ ሲመጣ ፡ ፊት ፡ ለፊቴ
|