ቅዱስ ፡ ሕዝብ ፡ በሚባረክበት (Qidus Hizb Bemibarekibet)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ቅዱስ ፡ ሕዝብ ፡ በሚባረክበት
ሌሊት ፡ በሚባራበት
ያ ፡ ብሩሕ ፡ ቀን ፡ ይምጣ ፡ ለፍጥረት
አውርድልን ፡ በረከት
በዚያን ፡ ጊዜ ፡ ስብሐት
ሊነገር ፡ ከአዕላፋት

ምሥራቅ ፣ ምዕራብ ፣ ደቡብ ፣ ሰሜን
እስኪደርስ ፡ ግዛትህን
ቶሎ ፡ በወንጌል ፡ አሠልጥን
የጥንት ፡ ተስፋን ፡ ምላልን
ዘርህ ፡ እጅግ ፡ ይበዛል
በአንተ ፡ ይባረካል

ልታነድ ፡ የመጣህለት
ቅዱሱን ፡ እሣት ፡ ግለጥ
አንቀላቅለው ፡ በዕውነት
ብርሃን ፡ ሙቀት ፡ እንዲሰጥ
የጠፉትን ፡ ልንወድ
ፍቅርህን ፡ በኛ ፡ አንድድ

ት ፡ ሰማለህ ፡ ስንለምን
እንኳ ፡ ቢዘገይብን
አሕዛብን ፡ ልታሳምን
የለም ፡ ለርስትህ ፡ ወሰን
ፀጋህን ፡ ለምታሳይ
ስብሓት ፡ ለአንተ ፡ በሰማይ