ቀሪ ፡ ዘመኔን ፡ ጌታ ፡ ባርከው (Qeri Zemenien Gieta Barkew)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ቀሪ ፡ ዘመኔን ፡ ጌታ ፡ ባርከው
ምን ፡ ያህል ፡ ይሆናል?
ባለፈውማ ፡ ብዙ ፡ ነገር
ሥጋዬ ፡ አበላሽቷል

ጉልበቴ ፡ በባዕድ ፡ ምድር ፡ ጣዖትን ፡ አክብሯል
የመንፈስ ፡ ቅዱስን ፡ ሥራ ፡ ሥጋዬ ፡ አበላሽቷል
ዓይኖቼ ፡ ወዳዩት ፡ ሁሉ ፡ እግሮቼ ፡ ሮጠዋል
ያለፈው ፡ ዘመኔ ፡ ሲታይ ፡ እጅግ ፡ ያሳዝናል

አዝ፦ ቀሪ ፡ ዘመኔን ፡ ጌታ ፡ ባርከው
ምን ፡ ያህል ፡ ይሆናል?
ባለፈውማ ፡ ብዙ ፡ ነገር
ሥጋዬ ፡ አበላሽቷል

አርነቴን ፡ ተከልዬ ፡ ብዙ ፡ ቀልጃለሁ
ፀጋህ ፡ ለእኔ ፡ ስለበዛ ፡ ሳውቅም ፡ በድያለሁ
አቤት! ምን ፡ ያህል ፡ ታጋሽ ፡ ነህ ፡ ከበደሌ ፡ በላይ?
እባክህ ፡ የቀረኝ ፡ ዘመን ፡ ፊትህ ፡ ከብሮ ፡ ይታይ

አዝ፦ ቀሪ ፡ ዘመኔን ፡ ጌታ ፡ ባርከው
ምን ፡ ያህል ፡ ይሆናል?
ባለፈውማ ፡ ብዙ ፡ ነገር
ሥጋዬ ፡ አበላሽቷል

በተቀደሰው ፡ መቅደስህ ፡ ደምን ፡ አፍስሻለሁ
አንተ ፡ የምትተክላትን ፡ ነፍስ ፡ እኔ ፡ ገድያለሁ
ዓለም ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ ስትተፋ ፡ ተባብሬያለሁ
ጌታ ፡ ባለፈው ፡ ዘመኔ ፡ ብዙ ፡ ባክኛለሁ

አዝ፦ ቀሪ ፡ ዘመኔን ፡ ጌታ ፡ ባርከው
ምን ፡ ያህል ፡ ይሆናል?
ባለፈውማ ፡ ብዙ ፡ ነገር
ሥጋዬ ፡ አበላሽቷል