ቀንዴ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ አለ (Qendie Kef Kef Ale)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኑሮዬ ፡ ያልተሳካልኝ ፡ ዕድለ ፡ ቢስ ፡ ነኝ ፡ እኔ
እያልኩኝ ፡ እኖር ፡ ነበር ፡ በዚህች ፡ ሕይወት ፡ ዘመኔ
ዛሬ ፡ ግን ፡ በኢየሱስ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ብሎ ፡ ቀንዴ
በምሥጋና ፡ ተሞላሁ ፡ አልፎ ፡ የችግር ፡ ዘመኔ

አዝቀንዴ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ አለ (፪x)
አፌም ፡ በጠላቶቼ ፡ ላይ ፡ ተከፈተ
ልቤም ፡ በእግዚአብሔር ፡ ጸና (፪x)
እስኪ ፡ ቆሜ ፡ ለጌታዬ ፡ ልሰዋ ፡ ምሥጋና (፪x)

የዕለት ፡ ምግቤን ፡ እንኳን ፡ ከሰው ፡ እየጠበኩኝ
ሰዎችን ፡ ተስፋ ፡ ሳደርግ ፡ በልመና ፡ ወደኩኝ
ዛሬ ፡ ግን ፡ በኢየሱስ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ብሎ ፡ ቀንዴ
ጐተራው ፡ ሁሉ ፡ ሞልቷል ፡ ረሃብ ፡ ጠፍቷል ፡ ከሆዴ

አዝቀንዴ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ አለ (፪x)
አፌም ፡ በጠላቶቼ ፡ ላይ ፡ ተከፈተ
ልቤም ፡ በእግዚአብሔር ፡ ጸና (፪x)
እስኪ ፡ ቆሜ ፡ ለጌታዬ ፡ ልሰዋ ፡ ምሥጋና (፪x)

አንገቴን ፡ አቀርቅሬ ፡ ተደፍቼ ፡ ሄጃለሁ
ደግሞ ፡ ለጠላቶቼ ፡ መሳለቂያ ፡ ሆኛለሁ
ዛሬ ፡ ግን ፡ በኢየሱስ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ብሎ ፡ ቀንዴ
ቀና ፡ ብዬ ፡ ተራመድኩኝ ፡ ተከፈተልኝ ፡ አፌ

አዝቀንዴ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ አለ (፪x)
አፌም ፡ በጠላቶቼ ፡ ላይ ፡ ተከፈተ
ልቤም ፡ በእግዚአብሔር ፡ ጸና (፪x)
እስኪ ፡ ቆሜ ፡ ለጌታዬ ፡ ልሰዋ ፡ ምሥጋና (፪x)

ለቅሶዬን ፡ ወደ ፡ ደስታ ፡ ጩኸቴን ፡ ወደ ፡ ሆታ
ማቄንም ፡ ባማረ ፡ ልብስ ፡ ለውጦልኛል ፡ ጌታ
ዛረ ፡ ግን ፡ በኢየሱስ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ብሎ ፡ ቀንዴ
ሁሉ ፡ ነገር ፡ አልፏል ፡ ይክበር ፡ መድሃኒቴ

አዝቀንዴ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ አለ (፪x)
አፌም ፡ በጠላቶቼ ፡ ላይ ፡ ተከፈተ
ልቤም ፡ በእግዚአብሔር ፡ ጸና (፪x)
እስኪ ፡ ቆሜ ፡ ለጌአዬ ፡ ልሰዋ ፡ ምሥጋና (፪x)