ቅዱስ ፡ ስም ፡ ብፁዕ ፡ ስም (Qedus Sem Betsue Sem)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ሐዘንተኛን ፡ ያጽናናው
የመድሃኒታችን ፡ ስም
ያንን ፡ ቅዱስ ፡ ስም ፡ የጠራ
ይረዳል ፡ ይድናልም

አዝ፦ ቅዱስ ፡ ስም ፡ ብጹዕ ፡ ስም
የዘለዓለም ፡ ተስፋ ፡ ነው

ብርቱ ፡ ጋሻም ፡ ይሁንለት
ኀጢአት ፡ ሲፈትነው
ልመናውም ፡ ይፈጸምለት
ከኢየሱስ ፡ የለመነው

አዝ፦ ቅዱስ ፡ ስም ፡ ብጹዕ ፡ ስም
የዘለዓለም ፡ ተስፋ ፡ ነው

ያ ፡ ክቡር ፡ የኢየሱስ ፡ ስም
ብጽዕናን ፡ ይሰጠናል
ሕይወት ፡ ደስታም ፡ ሰላምም
ከዚህ ፡ ስም ፡ አግኝተናል

አዝ፦ ቅዱስ ፡ ስም ፡ ብጹዕ ፡ ስም
የዘለዓለም ፡ ተስፋ ፡ ነው

ወደ ፡ ሰማያዊ ፡ አገር
አድኖ ፡ ሲያደርሰን
ያንን ፡ ስም ፡ ለአምላክ ፡ ክብር
እንዘምር ፡ እክብረን

አዝ፦ ቅዱስ ፡ ስም ፡ ብጹዕ ፡ ስም
የዘለዓለም ፡ ተስፋ ፡ ነው