ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ (Qedus Qedus Qedus)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ
ኃያል ፡ ጌታችን ፡ በየጧቱ
ለአንተ ፡ እንዘምራለን
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ
መሃሪ ፡ እና ፡ ኃያል ፡ እግዚአብሔር
የዘለዓለም ፡ ገዥ

ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ
መላእክት ፡ ያክብሩህ
ዘውዳቸውን ፡ በዙፋንህ ፡ ዙሪያ ፡ ትተው
አእላፋት ፡ በሰማይ ፡ ይሰግዱልሃል
አምላክ ፡ የነበርህ ፡ ያለህ ፡ የምትኖር

ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ
ክብርህ ፡ ቢጋረድ
ግርማህን ፡ የሰው ፡ ዓይን
ሊያየው ፡ ባይችልም ፡ እንኳ
ብሩክ ፡ አምላክ ፡ ቅዱስ ፡ ነህ
እንዳንተ ፡ አይገኝም
የተሞላህ ፡ በኃይል ፡ በፍቅር