ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ብለው ፡ መላዕክት ፡ ዘመሩ (Qedus Qedus Belew Melaekt Zemeru)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

በሰማይ ፡ መዝሙር ፡ ሲዘመር ፡ ሰምተነው ፡ የማናውቀው
መላዕክትም ፡ ሲያመሰግኑት ፡ በዙፋን ፡ ላይ ፡ ያለውን
በተቃኘው ፡ በገናቸው ፡ ባማረውም ፡ ድምጻቸው
ኦ ፡ እኛም ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስን ፡ ከልብ ፡ እናገልግለው

አዝ፦ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ብለው ፡ ሲዘምሩ
እኔም ፡ ተባብሬያቸው ፡ የሰማይን ፡ ቤት ፡ ላደምቅ
ግን ፡ የመዳን ፡ ታሪክ ፡ ስዘምር
ያዳምጣሉ ፡ መላዕክት
ከቶ ፡ አላወቁም ፡ የመዳንን ፡ ደስታ

ግን ፡ ሌላ ፡ መዝሙር ፡ ሰማሁ ፡ አስደሳች ፡ በሆነ ፡ ድምጽ
እኛን ፡ ላዳነን ፡ ጌታ ፡ ለገዛን ፡ ነው ፡ መዝሙሩ
መከራን ፡ ሁሉ ፡ ያለፍነው ፡ ወደዚያች ፡ ግሩም፡ አገር
በሚወርደውም ፡ ንጹሕ ፡ ምንጭ ፡ ልብሳችንን ፡ አነጻው

አዝ፦ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ብለው ፡ ሲዘምሩ
እኔም ፡ ተባብሬያቸው ፡ የሰማይን ፡ ቤት ፡ ላደምቅ
ግን ፡ የመዳን ፡ ታሪክ ፡ ስዘምር
ያዳምጣሉ ፡ መላዕክት
ከቶ ፡ አላወቁም ፡ የመዳንን ፡ ደስታ

መላዕክት ፡ ቆመው ፡ ሲሰሙ ፡ ያልዘመሩትን ፡ መዝሙር
እነዚያ ፡ በደም ፡ የነጹት ፡ በብዙ ፡ ፏፏቴ ፡ ድምጽ
ስለ ፡ መከራ ፡ ዘመሩ ፡ ድል ፡ የነሱትንም ፡ ውጊያ
ታላቁን ፡ አዳኝ ፡ ወደሱት ፡ ያመሰገናቸውን ፡

አዝ፦ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ብለው ፡ ሲዘምሩ
እኔም ፡ ተባብሬያቸው ፡ የሰማይን ፡ ቤት ፡ ላደምቅ
ግን ፡ የመዳን ፡ ታሪክ ፡ ስዘምር
ያዳምጣሉ ፡ መላዕክት
ከቶ ፡ አላወቁም ፡ የመዳንን ፡ ደስታ

እኔ ፡ ምንም ፡ መልዓክ ፡ ባልሆን ፡ ከዚያ ፡ ያለውን ፡ አውቃለሁ
አዝማቼን ፡ እዘምራለሁ ፡ መላዕክት ፡ ያልዘመሩትን
ላዳኜ ፡ እዘምራለሁ ፡ በጨለማው ፡ መስቀል ፡ ላይ
በደሌን ፡ ለደመሰሰው ፡ ከኃጢአቴም ፡ ላነጻኝ

አዝ፦ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ብለው ፡ ሲዘምሩ
እኔም ፡ ተባብሬያቸው ፡ የሰማይን ፡ ቤት ፡ ላደምቅ
ግን ፡ የመዳን ፡ ታሪክ ፡ ስዘምር
ያዳምጣሉ ፡ መላዕክት
ከቶ ፡ አላወቁም ፡ የመዳንን ፡ ደስታ