ቅዱስ ፡ ቃሉን ፡ የሚሰሙ (Qedus Qalun Yemisemu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ቅዱስ ፡ ቃሉን ፡ የሚሰሙ
አምላክን ፡ የሚወዱ
ታዘው ፡ ለቅዱስ ፡ ፍቃዱ
ለጌታ ፡ የሚለፉ
በመንፈሱ ፡ የሚመሩ
በእውነት ፡ ብፁዓን ፡ ሆኑ
መንግሥቱንም ፡ ሊወርሱ

እምነታቸው ፡ ድል ፡ ሊነሳ
ጠብ ፡ ሁከት ፡ በሚገዛ
ፍቅራቸው ፡ ደምቆ ፡ ሊነድድ
ፍቅር ፡ በዓለም ፡ ሲበርድ
የተስፋቸውም ፡ መሠረት
ፀንቷል ፡ እንደ ፡ አለት
በሞት ፡ ሆነ ፡ በሕይወት

ድሙቅ ፡ ጩራ ፡ ከአብ ፡ ግርማ
ይውረድ ፡ በምድር ፡ ዙርያ
ተንጀርግጐ ፡ ሊያፈራ
ቸርነት ፡ ሰላም ፡ ደስታ
በግርማ ፡ የምታጋባ
ይህች ፡ ምድር ፡ ትሁን ፡ ለእኛ
ሰማያዊ ፡ መግቢያ