ቀጭን ፡ ሆነች (Qechen Honech)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ቀጭን ፡ ሆነች ፡ የሕይወት ፡ ደጅ
ያች ፡ መንገድ ፡ ጠባብ ፡ ነች
ተጋደል ፡ አንተ ፡ የሰው ፡ ልጅ
በዚያ ፡ ለመግባት ፡ (፪X)

ሰማያት ፡ ገና ፡ አልሞሉም
ሥፍራ ፡ ገና ፡ አለ
ደጆቹ ፡ ስለ ፡ ኢየሱስ ፡ ስም
ለአንተ ፡ ተከፈቱ ፡ (፪X)

በአምላክ ፡ ፊት ፡ በሚቆሙ
ከብጹዓን ፡ ጋራ
አሳብሮ ፡ በምሕረቱ
አንተን ፡ ሊያገባ ፡ (፪X)

በኢየሱስ ፡ ቤት ፡ በገነቱ
አለ ፡ ገና ፡ ሥፍራ
ይጠራኛል ፡ በወንጌሉ
ወደ ፡ ሰማይ ፡ ደስታ ፡ (፪X)

በዚያ ፡ አገር ፡ በጸጥታ
ተመችቶኝ ፡ ልኖር
ብጹዕ ፡ እርሱ ፡ የሚሰማ
የአምላክን ፡ ምክር ፡ (፪X)