ኦ ፡ ርኅሩኅ ፡ አምላክ ፡ ፀጋህን ፡ ስጠነ (Oh Rihruh Amlak Tsegahin Sittene)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኦ ፡ ርኅሩኅ ፡ አምላክ ፡ ፀጋህን ፡ ስጠነ
ከኃጢአትም ፡ በእርሱ ፡ አድነነ
ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ መንፈስህንም ፡ ላክልኝ
በፊትህም ፡ ምሕረትህ ፡ ይቁምልኝ

የዓለም ፡ ብርሃን ፡ ጧቱ ፡ ኮከብ
የምድር ፡ ልጆችን ፡ ወዳንት ፡ ለማቅረ
ከወጣሁ ፡ አንተን ፡ እመለከታለሁ
በደስታም ፡ ጮራህን ፡ እከተላለሁ

በኃጢአት ፡ ዕንቅልፍ ፡ ለማንቀላፋት
ሞትም ፡ ልሞት ፡ አልተውኸኝም ፡ ኦ! አባት
በፀጋህ ፡ ስለሰጠህ ፡ ምሕረትን
ተቀበል ፡ ልቤን ፡ ገጸ ፡ በረከቴን

መድኃኒት ፡ ሆይ! ለእኔና ፡ ለሁሉ
የመቅሠፍት ፡ ጽዋን ፡ ጠጣኸው ፡ በምሉ
እወድሃለሁ ፡ በአንተም ፡ አምናለሁ
በኃይልህም ፡ ከውድቀት ፡ እድናለሁ