ኦ ፡ ነፍሴ ፡ ለአምላክሽ ፡ ተሰጪ (Oh Nefsie Leamlakesh Tesechi)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኦ ፡ ነፍሴ ፡ ለአምላክሽ ፡ ተሰጪ
ተስፋሽንም ፡ እርሱን ፡ አድርጊ
በትካዜም ፡ ስትበሳጪ
ረድዔትን ፡ ከእርሱ ፡ ፈልጊ
አምላክን ፡ የሚታመነው
ቤቱን ፡ አይሠራም ፡ በአሸዋው

የማጽናናት ፡ ወቅት ፡ ይመርጣል
ጥቅምህንም ፡ ያስባል
የምትለምነውን ፡ ይሰጣል
ቁዘማህም ፡ ይሰማዋል
ባልታሰበም ፡ ጊዜ ፡ ረድዔት
ይሰጥሃል ፡ በምሕረት

ችግርህ ፡ እንኳ ፡ ቢበረታ
አምላክ ፡ የጣለህ ፡ አይምሰልህ
ሐዘንን ፡ ይለውጣል ፡ በደስታ
ከሐዘን ፡ ደስታ ፡ ሲሻልህ
ሁል ፡ ጊዜም ፡ ይወድሃል
መዳንህንም ፡ ያስባል

ታላላቆቹን ፡ ዝቅ ፡ ለማድረግ
ለአምላካችን ፡ ቀላል ፡ ነው
ምስኪኖቹንም ፡ ማበልጠግ
ለርሱ ፡ የማያስቸግር ፡ ነው
ልዑል ፡ አምላክ ፡ በምክሩ
ያስገርማል ፡ መንክር ፡ ግብሩ