ኦ ፡ ነፍሴ ፡ አሁን ፡ ደስ ፡ ይበልሽ (Oh Nefsie Ahun Des Yibelish)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ኦ! ነፍሴ ፡ አሁን ፡ ደስ ፡ ይበልሽ
ኦ! ልቤ ፡ ሐሤት ፡ አድርጊ
በደሙ ፡ ኢየሱስ ፡ እንደገዛሽ
የሚለውን ፡ ወንጌል ፡ አትርሺ
አምላክሽ ፡ እንደወደደሽ
ሰው ፡ ሆኖ ፡ አንቺን ፡ እንደዋጀሽ

በከንቱም ፡ ፀጋውን ፡ እንደሰጠሽ
ይህንን ፡ ከቶ ፡ አትርሺ

በልቤ ፡ ጭንቅ ፡ ብቻ ፡ ቢሰማኝ
እንዳለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ገዝቶኛል
ማናቸውም ፡ ነገር ፡ ቢያስፈራኝ
የደሙ ፡ ቤዛ ፡ በቅቷል
ድሃ ፡ ብሆን ፡ ብከብርም
ብቸገርም ፡ ደስታ ፡ ባገኝም
በሕይወት ፡ ዘመኔም ፡ በሞትም
የኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ገንዘብ ፡ ነኝ

በኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ የሚያምን
ከሌላ ፡ ሁሉ ፡ ታደለ
በኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ደም ፡ ሰላምን
ከአምላኩ ፡ ተቀበለ
በአባት ፡ ፍቅር ፡ ያየዋል
በመንገዱም ፡ ወትሮ ፡ ይመራል
ልጁንም ፡ ወደ ፡ ላይ ፡ ይጠራል
ለዚህም ፡ ኢየሱስ ፡ ገዝቶታል