ኦ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ና ፡ ወደኔ (Oh Menfes Qdus Na Wodenie)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኦ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ና ፡ ወደኔ
ልቤንም ፡ ክፈት ፡ ለአንተ
በዕውነቱ ፡ የምትመራ
በዕውነት ፡ ልቤንም ፡ ምራ

የኃጢአት ፡ ጸጸት ፡ ሲሞርደኝ
ፍርሃት ፡ ጭንቀትም ፡ ሲያውከኝ
በምሕረትህ ፡ ነህ ፡ የምታድል
ሰላምም ፡ ነዋሪም ፡ ዕድል

ከክፉ ፡ ምኞት ፡ ነፍሴን ፡ አንጻ
የጨለመ ፡ ልቤን ፡ አብራ
ንገሥ ፡ በእርሱ ፡ በቅድስና
ምላበት ፡ ያን ፡ ቅዱስ ፡ ደስታ

ጠማማ ፡ ፈቃዴንም ፡ አቅና
ቅናትም ፡ በልቤ ፡ አግባ
ለአምላክ ፡ ክብረት ፣ ለሰውም ፡ ጥቅም
እርዳኝ ፡ ለመኖር ፡ በዓለም