ኦ ፡ ግሩም ፡ ጊዜ ፡ ኦ ፡ ብሩክ ፡ ሰዓት (Oh Grum Gizie Oh Bruk)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ


ኦ ፡ ግሩም ፡ ጊዜ ፡ ኦ ፡ ብሩክ ፡ ሰዓት ለቅዱሣን ፡ ለነቢያት የታየው ፡ ቀን ፡ መጣልን አሁንም ፡ እንደ ፡ ዓብ ፡ ሥምረት የአምላካችን ፡ ምሕረት ወደኛ ፡ ወረደልን ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ሰው ፡ ሆነልን እናመስግን ፡ በአንድነት እንወድሰውም ፡ በዕምነት

እንደ ፡ ዓብ ፡ በፍፁም ፡ አምላክ ፡ ነው እንደኛም ፡ ሆነ ፡ ፍፁም ፡ ሰው ወዳምላክ ፡ ሊያቀርበን የጠፉትን ፡ ይፈልጋል ሰላሙንም ፡ ይሰጠናል መድኃኒትም ፡ ሆነልን ጥፉን ፡ ልጁን ፡ እንዲያድን የዓብ ፡ ፈቃድን ፡ ለመፈጸም ወልድ ፡ ተገለጠ ፡ በዓለም

በመከራችን ፡ አልቅሶ ጭንቃችንን ፡ አስታውሶ በመንፈሱ ፡ ሊጦረን የዓብንም ፡ ፈቃድ ፡ ሊገልጥ ከጭንቅም ፡ ሁሉ ፡ የሚበልጥ ምሉዕ ፡ ረድዔት ፡ ሊሆነን በሞት ፡ ሕይወት ፡ ሊዋጅልን የሞት ፡ ጻርን ፡ ታግሦልን ይከፍትልናል ፡ ሰማይን

ሊያድነነ ፡ መጥቷል የፀጋም ፡ ጀንበር ፡ ወጥቷል ከቶ ፡ የማይተወነ እርሱን ፡ እንድንከተለው በዕውነት ፡ እረኛችን ፡ ነው ገንዘቡም ፡ እኛ ፡ ነነ በእርሱም ፡ ተስፋ ፡ አለነ እንዲሰጠን ፡ ግሩም ፡ ብጽዕና ለርሱ ፡ ነው ፡ የሰው ፡ ምሥጋና