ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ የሕይወት ፡ ውሃ (Oh Eyesus Yehiwot Wuha)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ የሕይወት ፡ ውሃ
የፀጋ ፡ ምንጭ ፡ ሆንህልኝ
ልቤ ፡ የለመነውን ፡ ስማ
በፀጋም ፡ ፈጽምልኝ
ታላቅ ፡ ፍቅርህ ፡ ግሩም ፡ ስምህም
የከፈትህልኝ ፡ ዕቅፍህም
ለነፍሴ ፡ ድፍረት ፡ ሰጠ

ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ወደ ፡ መስቀልህ
እጄን ፡ እዘረጋለሁ
ዓይኔንም ፡ ወደ ፡ ምሕረትህ
በተስፋ ፡ አነሣለሁ
የዕውቀት ፡ ዛፍ ፡ ያፈራውን ፡ ፍሬ
በመስቀል ፡ ዛፍ ፡ ኦ ፡ መድኅኔ
ከለቀምኸው ፡ ጠፋልኝ

ተመስገን ፡ ቸር ፡ መድኃኒቴ
ፍርዴን ፡ ተሸከምህልኝ
በማይመረመር ፡ ርኅራኄ
ሞቴን ፡ ተቀበልህልኝ
ያጠፋሁትን ፡ ከፈልኸው
ሰማይን ፡ ለእኔ ፡ ከፈትኸው
ስምህን ፡ እንዳከብር

ዓይኔም ፡ ሲዘጋ ፡ አካሌም
ወደ ፡ መሬት ፡ ሲመለስ
ከመከራ ፡ ከትካዜም
ድኜ ፡ አንተን ፡ ልወድስ
ለዓብ ፣ ለወልድ ፣ ለመንፈስም
ይሁን ፡ ምሥጋና ፡ ውዳሴም
እስከ ፡ ዘለዓለም ፣ አሜን