ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ቃልህ ፡ ጸንቷል (Oh Eyesus Qalih Tsentoal)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ቃልህ ፡ ጸንቷል
መንግሥትህም ፡ አይፈርስም
ጠላትህ ፡ ይወረውራል
ወደ ፡ አምባህ ፡ ግን ፡ አይደርስም
እስከ ፡ ዘለዓለም ፡ እንዳይወድቅ
አንተ ፡ በዕውነትና ፡ ጽድቅ
ዙፋንህን ፡ አጸናህ

ለእኛ ፡ ግን ፡ ቶሎ ፡ የሚያልቅ
የጠፋም ፡ ይመስለናል
መሠረቱም ፡ እንደሚወድቅ
መስሎን ፡ ደንገጥ ፡ ይለናል
ይህ ፡ ግን ፡ ኃይልህ ፡ ባይሰማን ፡ ነው
መንግሥትህ ፡ የማይጠፋ ፡ ነው
ቃልህም ፡ ይረጋጋል

ግን ፡ ጌታ ፡ ሆይ! የአንተ ፡ ሥልጣን
ከዚህ ፡ ዓለም ፡ አይደለም
ከምድር ፡ ሁሉ ፡ ክቡራን
የሚሰግድልህ ፡ የለም
የክርስቲያኖችህ ፡ ድካም
ሲታይ ፡ የመንግሥትህ ፡ ሰላም
ለዓለም ፡ ሰው ፡ አይታይም

ተመስገን ፡ ርኅሩሕ ፡ መድኅኔ
ለእኔ ፡ ተገለጠልኝ
የመንግሥትህ ፡ ወራሽ ፡ ሆኜ
ብጽዕናህ ፡ ደረሰልኝ
ከአንተም ፡ ዘንድ ፡ ምሥጋናህን
ስዘምር ፡ ታላቅ ፡ ፀጋህን
ዘለዓለሙ ፡ ላመስግን