ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ከእኔ ፡ ተባበር (Oh Eyesus Kenie Tebaber)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ከእኔ ፡ ተባበር
የሚጐዳውን ፡ አባርር
ወደ ፡ አንተ ፡ ተማጥኜ
ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ሠርክ ፡ ሁን ፡ ከእኔ

ኢየሱስ ፣ ከእኔ ፡ ዘንድ ፡ ከሆንህ
ነፍሴን ፡ በፀጋህ ፡ ከጦርህ
አንድ ፡ አይጐድልም ፡ ለእኔ
ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ሠርክ ፡ ሁን ፡ ከእኔ

ከዚህች ፡ ዓለም ፡ ስሰናበት
በሰማይ ፡ አግባኝ ፡ በምሕረት
ላቅርብልህ ፡ ውዳሴ
ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ሠርክ ፡ ሁን ፡ ከእኔ