ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ አምላኬ (Oh Eyesus Amlakie)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ አምላኬ
ለቃልህ ፡ ታዝዤ
ወደ ፡ አንተ ፡ እቀርባለሁ
ፀጋህንም ፡ እሻለሁ
በደምህ ፡ ሕሊናዬ
ይረጭ ፡ ከኃጢአቴ

ዘለዓለም ፡ የአንተ ፡ ነኝ
የሚል ፡ ዕምነት ፡ ስጠኝ
ከአንተም ፡ ከሚለየኝ
ልርቅ ፡ ረድዔት ፡ ሁንልኝ
ሞትም ፡ በማይደርስብኝ
በመንግሥትህ ፡ አኑረኝ