ኦ ፡ አምላኬ ፡ በኃጢአቴ (Oh Amlakie Behattiyatie)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ኦ ፡ አምላኬ ፡ በኃጢአቴ
መንፈሴ ፡ አዘነብኝ
በዚች ፡ ዓለም
አንድ ፡ ሰው ፡ የለም
በጭንቀት ፡ የሚረዳኝ

ሩቅም ፡ ብሄድ
ረጅም ፡ መንገድ
እስከ ፡ ዓለም ፡ ዳርቻ
በየት ፡ ላገኝ
ደስ ፡ የሚለኝ
ከሃዘን ፡ የሚፈታ

ወደ ፡ አንተ
ቸር ፡ አምላኬ
እቀርባለሁ ፡ አሁን
አባት ፡ ሁነኝ
ተዓገሠኝ
ዘወትር ፡ ሁንልኝ ፡ ተገን

ቸር ፡ ኢየሱስ
ልሆን ፡ ዕጉሥ
አድስ ፡ ክፉ ፡ ጠባዬን
ደካማ ፡ ነኝ
አራምደኝ
በደስታ ፡ ወይ ፡ በሃዘን

በአንተ ፡ ፈቃድ
በቅን ፡ መንገድ
ልሄድ ፡ እጄን ፡ ያዝልኝ
በዚች ፡ ዓለም
ብርቱ ፡ ሸክም
ልታገስ ፡ ኃይልን ፡ ስጠኝ

ዓብና ፡ ወልድ
በባሕርይ ፡ አንድ
ከመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ጋራ
ስማኝ ፡ አሁን
አዎን ፡ አሜን
ጸሎቴን ፡ ልትሰማ