ኦ ፡ አባት ፡ ኦ ፡ መድኃኒታችን (Oh Abat Oh Medhanitachen)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኦ ፡ አባት ፡ ኦ ፡ መድኃኒታችን
በፀጋህ ፡ ኃይል ፡ ወደኛ ፡ ና
ፍቅርህም ፡ በመካከላችን
የመንፈስህን ፡ ብርሃን ፡ ያብራ

ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ና ፡ ወደ ፡ ሁላችን
ናና ፡ በፍቅርህ ፡ አሙቀን
በአንተም ፡ እንዲሆን ፡ ተስፋችን
ምሕረትህን ፡ አስታውቀን

ይጥፋ ፡ የሚያታልል ፡ ተስፋ
ሰነፉም ፡ ምንጭ ፡ ይድረቅ ፡ አሁን
መዳን ፡ የማይሰጥ ፡ ጥግም ፡ ይጥፋ
አምባችን ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ሁን

ውዳሴ ፣ ክብር ፣ ኃይል ፣ ምሥጋና
ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ይገባል
በቅልህም ፡ እንድንጸና
ተስፋችን ፡ አንተ ፡ ሁነሃል