ኦ ፡ ቸር ፡ መድኃኒቴ ፡ አንተን ፡ እንዴት ፡ ላመስግን (Oh! Cher Medhanite Anten Endiet Lamesgin)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ኦ ፡ ቸር ፡ መድኃኒቴ ፡ አንተን ፡ እንዴት ፡ ላመስግን?
በቅዱስ ፡ ምሥጢርህ ፡ አበላኸኝ ፡ ሥጋህን
ለልቤም ፡ አዲስ ፡ ኃይል ፡ ከደምህ ፡ ሰጠኸኝ
ከአንተ ፡ ተባብሬ ፡ በፀጋህ ፡ ብፁዕ ፡ ነኝ

የኃጢአቴን ፡ ፍርድ ፡ ከእኔ ፡ አነሣህልኝ
ወደኔም ፡ መጥተህ ፡ በፍቅርህ ፡ ታየህልኝ
ደካማ ፡ ዕምነቴን ፡ በፀጋህ ፡ ጨመርኸው
በመስቀልህም ፡ ኃይል ፡ ነፍሴን ፡ አጸናኸው

ገንዘብህ ፡ እንድሆን ፡ በመስቀል ፡ የሞትህልኝ
ኦ! ግሩም ፡ መድኃኒቴ ፡ የሕይወት ፡ ምንጭ ፡ ሆንህልኝ
ብፅዕናን ፡ እንድወርስ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ቆይ
አንተ ፡ ነህ ፡ ሕይወቴ ፡ ኦ! ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ሆይ!